🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ማስታወቂያ ራይት ናው ሚዲያ :- ቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን ለሁሉም የቤተክርስቲያን አባላት | Beza International Church

ማስታወቂያ

ራይት ናው ሚዲያ
:- ቤዛ ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን ለሁሉም የቤተክርስቲያን አባላት የራይት ናው ሚዲያ ደንበኝነት ገዝታለች። ራይት ናው ሚዲያ ልክ እንደ ኔትፍሊክስ ከ20,000 በላይ ነፃ የክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቪዲዮዎችንና 2,000 የሚሆኑ የልጆች ቪዲዮዎች ያለው ቪዲዮዎችን ለማየት የሚያስችል አገልግሎት ነው። እነዚህ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ቪዲዮዎች በኢሜል በመመዝገብ ማግኘት ይችላሉ። ይዘቱ እርስዎ እና ቤተሰብዎ በሳምንቱ ውስጥ አእምሮዎን ለማደስ እና ቤተሰብዎን ደቀመዝሙር ለማድረግ እንዲረዳ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥሩ ትምህርት አለው። እንደ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ የክርስቲያን ኑሮ፣ ነገረ መለኮት፣ ወላጅነት፣ የአእምሮ ጤና እና ሌሎችም ርዕሰ ጉዳዮች አሉት። በማንኛውም ኤሌክትሮኒክ ላይ የሚሰራ ሲሆን እንደ ስማርት ቲቪ ባሉ መሳሪያዎች እንደ ቤተሰብ ሆነው ለማየት ወይም በማንኛውም ቦታ ላይ ሆነው በስልክዎ ማየት ላይ ይችላሉ።

በኢሜልዎ መላክ ሳያስፈልጋችሁ ለራይት ናው ሚዲያ በቀጥታ መመዝገብ የምትችሉበትን ሊንክ ሊንክትሪ ላይ አስገብተነዋል። ስለዚህ አገናኙን በመጫን መለያዎን እና የይለፍ ቃልዎን መፍጠር ትችላላችሁ። በኢሜልዎ ልከንሎት ነገር ግን ግብዣው ካልደረሰዎት እባክዎን spam ወይም promotions የሚለው የመልእክት ሳጥን ውስጥ በመግባት ያረጋግጡ።

ለ ራይት ናው ሚዲያ ነፃ የደንበኝነት ምዝገባ ለማግኘት እባክዎ በቀጥታ ከዚህ በታች ያለው ሊንክ ላይ ኢሜልዎን በመላክ ይመዝገቡ።

https://app.rightnowmedia.org/join/beza

እንዲሁም በ Linktree አድራሻችን፡ https://linktr.ee/BezaChurch ላይ ልታገኙት ትችላላችሁ።

ጾም ፀሎት:- ጳጉሜ 1 – 3 የጌታን ፊት የምንፈልግበት እና አዲሱን አመት በመንፈስ የምንቀበልበት የ3 ቀን የጾም ፀሎት ፕሮግራም ይኖረናል። ቀኑን ያዙት፣ በዚሁ በቤተክርስቲያን ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ እንገናኝ።

የአዲስ ዓመት ዋዜማ:- ቅዳሜ ጳጉሜ 5 ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ የአዲስ ዓመት ዋዜማ ፕሮግራማችን በዚሁ በቤተክርስቲያን እናከብራለን። የሁሉቱም አገልግሎቶች የጋራ ፕሮግራም ይሆናል። የዓመቱ መጨረሻ ስጦታችንን የምንሰጥበት ጊዜ ስለሚሆን በተዘጋጀ ልብ ለማክበር ኑ።

የአዲስ ዓመት ቀን:- እሁድ ጥዋት ከጠዋቱ 4 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ድረስ የጋራ ፕሮግራም ይኖረናል። ስለዚህ በመደበኛው ሰዓት ሳይሆን ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ኑ።

የቢሲዲኤ አገልግሎት:- ለአዲሱ አመት የትምህርት ዘመን 2015 ዓ.ም ትምህርት ለመጀመር የእኛን እገዛ የሚፈልጉ 650 ልጆች አሉን። የአንድን ልጅ የትምህርት ወጪ ለመሸፈን 1 500 ብር/ $ 30 ያስፈልገናል።

የሚያስፈልጉ ነገሮች፡
የትምህርት ቁሳቁስ (ደብተር፣ እስኪርቢቶ….) በአንድ ልጅ- 500 ብር
የጀርባ ቦርሳ በአንድ ልጅ- 500 ብር
ጫማ በአንድ ልጅ- 500 ብር

በእነዚህ የባንክ አካውንቶች በመጠቀም ገንዘብ ገቢ ማድረግ ይችላሉ
የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ- 1000008963642
አቢሲኒያ ባንክ- 9638105

T412
:- ከ12-14 ዓመት ያሉ የልጆች አገልግሎት፦ ነሀሴ 28 ቀን የህፃናት ማሳደጊያን ለመጎብኘት አቅደናል። ፕሮግራማችን ሙሉ ቀን ይሆናል እንዲሁም ፈቃደኛ የሆኑ ወላጆች መሳተፍ ይችላሉ። አውቶቡስ ይዘጋጃል ስለዚህ ታበርናክል ጠዋት 2፡30 ላይ እንገናኝ።

የደቀመዝሙር ትምህርት:- አዲስ ዙር እየተጀመረ ስለሆነ ያልተጠመቃችሁና መማር የምትፈልጉ ይህንን ትምህርት ከዛሬ ጀምሮ በመመዝገብ እንድትማሩ እናበረታታችኋለን፡፡

የአምልኮ ሰዓት:- የእሁድ የአምልኮ ሰዓት፦

የአማርኛ አገልግሎት፦ ከ2:45 - 4:45
የእንግሊዝኛ አገልግሎት፦ ከ5:15 - 7:15

የልጆች የሰንበት ትምህርት ፕሮግራም ፦

ዕድሜያቸው 2 እስከ 3 - ከአምልኮ በኋላ ወዲያውኑ ይጀምራል
ዕድሜያቸው 4 እስከ 11 - በ3:15 ሰዓት ይጀምራል
ዕድሜያቸው 12 እስከ 14 እድሜ - በ2፡45 ሰዓት ይጀምራል

የወጣቶች ፕሮግራም:- የቤዛ የወጣቶች ፕሮግራም ዕድሜያቸው ከ 15-23 ለሆኑ በየሳምንቱ እሁድ በአዲሱ ሕንጻ ቤዝመንት ከ 2፡45-4፡45 ይካሄዳል።

የደቀመዝሙርነት ትምህርት:- የደቀመዝሙርነት ትምህርት እሁድ በታበርናክል ከጠዋቱ 4፡45 እስከ 5፡45 ሰዓት ይካሄዳል። እሁድ መውሰድ የማይችል ማንም ሰው የደቀመዝሙርነት ትምህርት መውሰድ ከፈለገ በሌሎቹ ቀናት ፕሮግራም ስለምናዘጋጅ የምትፈልጉ እባካችሁ በዚህ ቁጥር "0907700007" አጭር የጽሑፍ መልክት በመላክ ወይም በዚህ የቴሌግራም አድራሻ "@bezaconnect" ይመዝገቡ።

ያልተለመደ ፀሎት ላለፈው ወር በርትቶ እየቀጠለ ነው። በቤዛ ቤተክርስቲያን የተጀመረው የፀሎት እንቅስቃሴ በየሳምንቱ እየቀጠለ ስለሆነ ይምጡና ለሃገራችንና ለተለያዩ ጉዳዮች ማልዱ። በአዲሱ ህንፃ ምድር ቤት ለፀሎት በተዘጋጀው አዳራሽ ውስጥ እየተካሄደ ነው።
ያልተለመደ ፀሎት መርሃ-ግብር፦

ሐሙስ - ክቀኑ 9 ሰዓት - 11 ሰዓት
ዓርብ - ከቀኑ 5:30 ሰዓት - 8:30 ሰዓት (የእህቶች ፕሮግራም)
ዓርብ - ከቀኑ 10 ሰዓት - ምሽቱ 1 ሰዓት (የእንግሊዘኛ ፕሮግራም)
ቅዳሜ ከጠዋቱ 1 ሰዓት-2 ሰዓት በቴሌግራም (ለመግባት በቴሌግራም ቻናላችን (@bezachurch) ከላይ JOIN የሚለውን በመጫን በቀላሉ ፀሎቱን መቀላቀል ትችላላችሁ።)
እሁድ - ከጠዋቱ 1:30 ሰዓት – 2:30 ሰዓት

የአንድ ብሎኬት ለሕንፃው ፕሮጀክታችን ተጀምሯል፡፡ ከአሁድ ፕሮግራም ስትወጡ በ50 ብር ከተዘጋጁት ብሎኬቶች በመግዛት ራዕዩን ወደ ፍፃሜ እናምጣው፡፡