Get Mystery Box with random crypto!

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል። የ | Bina Addis Consultancy

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል።

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን አገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ አስታወቀ።

የአገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ፤ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ከጥቅምት 29 እስከ ህዳር 2 ቀን 2014 ዓ.ም ይሰጣል ብለዋል።

የመፈተኛ ወይም የአድሚሽን ካርድ ከመስከረም 24 እስከ 26 ቀን 2014 ዓ.ም ለተማሪዎች እንደሚሰጥም ገልፀዋል።

ከ618 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀመጡ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ለዚህም ፈታኝ መምህራንን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን በማሟላት በቂ ዝግጅት ተደርጓል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia