Get Mystery Box with random crypto!

2ኛ ነገሥት 4 38፤ ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልገላ መጣ፥ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ል | Blaze Movement

2ኛ ነገሥት 4
38፤ ኤልሳዕም ዳግመኛ ወደ ጌልገላ መጣ፥ በምድርም ላይ ራብ ነበረ፤ የነቢያትም ልጆች በፊቱ ተቀምጠው ነበር፥ ሎሌውንም፡— ታላቁን ምንቸት ጣድ፥ ለነቢያት ልጆችም ወጥ ሥራ፡ አለው።
39፤ አንዱም ቅጠላቅጠል ያመጣ ዘንድ ወደ ሜዳ ወጣ፥ የምድረበዳውንም ሐረግ አገኘ ከዚያም የበረሀ ቅል ሰበሰበ፥ ልብሱንም ሞልቶ ተመለሰ፥ መትሮም በወጡ ምንቸት ውስጥ ጨመረው፤ ምን እንደ ሆነ ግን አላወቁም።
40፤ ሰዎቹም ይበሉ ዘንድ ቀዱ፤ ወጡንም በቀመሱ ጊዜ፡— የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ በምንቸቱ ውስጥ ሞት አለ፡ ብለው ጮኹ፤ ይበሉም ዘንድ አልቻሉም።
41፤ እርሱም፡— ዱቄት አምጡልኝ፡ አለ፤ በምንቸቱም ውስጥ ጥሎ፡— ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ቅዱ፡ አለ። በምንቸቱም ውስጥ ክፉ ነገር አልተገኘም።