Get Mystery Box with random crypto!

ለኦርቶዶክስ እና ለፕሮቴስታንት አማኞች ኢየሱስ ክርስቶስ በየቀኑ ወደ አብ ቀኝ እየቀረበ ይለምንልን | Blaze Movement

ለኦርቶዶክስ እና ለፕሮቴስታንት አማኞች
ኢየሱስ ክርስቶስ በየቀኑ ወደ አብ ቀኝ እየቀረበ ይለምንልን (ይማልድልን) ይሆን? በፍጹም!

ለኦርቶዶክስ እና ለፕሮቴስታንት አማኞች
ኢየሱስ ክርስቶስ በየቀኑ ወደ አብ ቀኝ እየቀረበ ይለምንልን (ይማልድልን) ይሆን? በፍጹም!

ኦርቶዶክሶች ፕሮቴስታንቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ይማልዳል ሲሉ የሚያስቡት ከትንሳኤም በኃላ ወልድ በአብ ቀኝ ሆኖ ወደ አብ በየቀኑ ይለምናልናል (ይማልዳልናል) የሚለውን ነው፡፡ ከብዙ ኦርቶዶክሶች ጋር ባደረኩት ውይይት እንደተረዳሁት እኛ የምንለውን ባለማብራራታችን እንዳልገባቸው እና እኛም ፕሮቴስታንቶች አብዛኞቻችንን ያማልዳል ከማለት ውጪ ገልጠን መጽሐፍ ቅዱስ አረዳዱን ማስረዳት አለመቻላችን ትልቅ ክፍተትን ፈጥሯል፡፡
ኦርቶዶክሶች ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ራሱን በመሰዋት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን የጠብ ግድግዳ ያፈረሰ መካከለኛ መሆኑን ያምናሉ፡፡ በምድር እያለ በመስቀል ላይ እንደማለደ ኢሳ 53፡12 ላይ እንዳለው ቃል መሰረት ‹‹…ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና ከአመፀኞችም ጋር ተቆጥሯልና እርሱ ግን የብዙዎችን ኃጢአት ተሸከመ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ፡፡›› በሚለው ቃል መሰረት በመስቀል ላይ መማለዱን ያምናሉ፡፡ በመሆኑም ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ በመስቀል መስዋዕት በመሆን፤ መስዋዕት አቅራቢው ሊቀ-ካህናት እርሱ፤ መስዋዕቱም እርሱ፤ መስዋዕት አሳራጊውም እርሱ፤ መስዋዕቱን ተቀባዩም /ይቅር ባዩም/ እርሱ ራሱ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ይህም መስዋዕት አንድ ጊዜ ለዘላለም የቀረበ መሆኑን እና ፍጹም በመሆኑም እንደ ኦሪት ካህናት መስዋዕት አይደማይደገም፤ እንደማይከለስም ያምናሉ፡፡ ይሄ በእርግጥም ንጹህ ወንጌል ነው፡፡
በተጨማሪም ዩሐ.16፡26 ላይ ‹‹በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለእናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ እራሱ ይወዳችኃልና›› በሚለው ጥቅስ መሰረትም ወደ አብ ቀኝ ካረገ በኃላ ምንም አይነት ልመናን (ምልጃ) እንደማያቀርብ ጥቅሱ በግልጽ ይናገራልና በአብ ቀኝ ሆኖ ልመናን አያቀርብም በሚል አይማልድም በሚል ይደመድማሉ፡፡ እኛም በተመሳሳይ በአብ ቀኝ ከገባ በኃላ አዲስ ልመናን አያቀርብም ብለን ብናምንም አይማልድም ብለን ግን አንደመድምም፡፡ ምክንያቱም ዕብ.7፡25 ላይ ‹‹ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል፡፡›› የሚለውን ጥቅስ መሻር አንችልምና! ታዲያ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው ስንል ምን ማለታችን ነው? በአብ ቀኝ ከገባ በኃላ አይለምንም እስከሚለው ከኦርቶዶክሶች ጋር ከተስማማን አሁንም በአብ ቀኝ ሰለእኛ ሊያማልድ በሕይወት ይኖራል ቃሉ ሲል እኛም ስንቀበል መረዳቱ እንዴት ነው የሚለው ቃሉ ብሏልና ሊፈታ እና ሊገባን ይገባል፡፡ አንደኛውን ቃል ለማጽናት ስንል ሌላኛውን ቃል አንሽረውምና!
አየሱስ ክርስቶስ በጎልጎታ በመስቀል ላይ እንደማለደ ሁላችንም (ኦርቶዶክሱም ፕሮቴስታንቱም) እናምናለን፡፡ ይህ የመስቀሉ የመማለድ ስራ ለዘለአለም ያማልዳል ብሎ በመስቀሉ ስራ መታመን ኦርቶዶክሶች እንደሚመስላቸው በየቀኑ ወደ አብ እየገባ ይለምናል ማለት አይደለም።
ኢየሱስ ከሞት ባይነሳ እና ደሙን ይዞ ወደ አብ ቀኝ ባይገባ መስቀል ላይ የማለደልን ምልጃ ፍጻሜውን አያገኝም ነበር። በራሱ ደም በትንሳኤ አካል ተነስቶ ሕያው ሆኖ እንደሊቀካህን በራሱ ደም ወደ ሰማያዊቷ ቅድስተ ቅዱሳን እኛን ወክሎ አንዴ ሲገባ በዚህ የማስታረቅ አገልግሎት በሆነው በመስቀል ላይ በተሰራው የመማለድ ስራ ለሚመካ ሊቀካህኑ በሕይወት እስካለበት ዘመን ሁሉ ክህነቱ ከመኃላ ጋር ይሰራል፡፡ ኢየሱስ መስዋዕት የመሆንና ወደ ሰማያዊቷ ቅድስተ ቅዱሳን በገዛ ደሙ የመግባትን የሊቀካህንነት ስራውን ጨርሶ በአብ ቀኝ እንደ መልከጸዴቅ ሹመት ከመኃላ ጋር ተወክሎልናል።
ኦርቶዶክሶች ግን ሊቀካህንነቱ ምድር ላይ እንዳበቃ አሁን ሊቀካህናችን ነው ብንል አንድ የኦርቶዶክስ ጸሐፊ እንዳለው ‹‹በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ ኢየሱስ ዛሬም በክህነት ያገለገላል ብሎ ማመን የቀራንዮ መስዋዕቱንና የክህነት አገልግሎቱን ከንቱ ማድረግ ነው!›› እንዳለው አይማልድም ብለው ያምናሉ፡፡ ነገር ቃሉ በዕብ.5፡8-10 ‹‹ምንም ልጅ ቢሆን ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኃላ በእግዚአብሔር እንደ መልከጸዴቅ ሹመት ሊቀካህናት ተብሎ ስለተጠራ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘለአለም መዳን ሆነላቸው፡፡›› ይላል፡፡ ኦርቶዶክሶች ኢየሱስ አሁንም ሊቀካህናችን እንደሆነ የማይቀበሉት ለመማለድ አሁንም መለመን ያስፈልገዋል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን ቃሉ ኢየሱስ እንደ መልከጸዴቅ ሹመት ሊቀካህን የሆነው መከራው ከተፈጸመ በኃላ እና ለዘለአለም ጭምር እንደሆነ ይነግረናል፡፡ ኦርቶዶክሶች ሊረዱ የሚገባቸው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በመማለድ ይህንን መስዋዕት ወደ አብ ቀኝ ይዞ የገባ እና የክህነት ስራው የተጠናቀቀ እና መስዋዕቱ ተቀባይነት አግኝቶ እግዚአብሔር በኢየሱስ የማስታረቅ አገልግሎት መርካቱን ሲሆን ይህ የመማለድ ስራ እውቅና በማግኘቱ ከመኃላ ጋር ለዚህ የመስቀሉ ስራ(ስም) ከስሞች ሁሉ በላይ የሆነውን ስም በመስጠት በሊቀካህነት ሹመት አጽድቆታል፡፡ ስለዚህ በአብ ቀኝ ሆኖ አሁን አይለምንም የሚለው ቃል ለመቀበል ሲባል ይሄን ቃል መሻር አያስፈልግም፡፡ በእርግጥም ወደ አብ ቀኝ ከገባ በኃላ ልመናን እንደማያቀርብልን ቃሉም ብሎናል እኛም እናምናለን፡፡ ልመና አያቀርብም የተባለውም አንድ ጊዜ መስቀል ላይ በኢየሱስ (በሊቀካህኑ) የተሰራው የመማለድ ስራ ሊቀካህኑ በህይወት ባለበት(ለዘለአለም) ለሚታመንበት የመማለድን ስራ ይሰራልና ነው፡፡ በመስቀሉ ስራ መታመን ማለትም ይህ ነው፡፡
ይሄንን ቃል እስቲ በድጋሚ በጥንቃቄ እናንብበው፡፡
ዩሐ.16፡26 ላይ ‹‹በዚያን ቀን በስሜ ትለምናላችሁ፤ እኔም ስለእናንተ አብን እንድለምን የምላችሁ አይደለሁም፤ እናንተ ስለወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ እራሱ ይወዳችኃልና››