Get Mystery Box with random crypto!

በተጨማሪም ጌታን ከተቀበልን በኃላ እንኳን በመንፈስ ሳንመራ ቀርተን ኃጢአት እንኳን ብንሰራ ከአብ | Blaze Movement

በተጨማሪም ጌታን ከተቀበልን በኃላ እንኳን በመንፈስ ሳንመራ ቀርተን ኃጢአት እንኳን ብንሰራ ከአብ ዘንድ ጠበቃ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳለን ቃሉ ስለሚል እኛም በዚህ ስንታመን በመስቀል ላይ አንዴ የተሰራልን ኃጢአትን ድል የማድረግ የመስቀሉ ስራ(ስሙ)(ኢየሱስ ክርስቶስ) ጠበቃ ሆኖ የዲያቢሎስን ክስ ድል እንደሚያደርግልን የሚገልጽ እና ያ የመስቀሉ የመማለድ ስራ በስሙ ስንጸልይ አሁንም ሕያው ሆኖ (ትኩስ ሆኖ) ለሰራነው ኃጢአት ዛሬም ስለሚማልድልንና ከየትኛውም ክስ ስለሚከራከርልንና ነጻ በማውጣት ከኃጢአታችን ስለሚያነጻንና ዲያቢሎስን ስለሚያሳፍረው ነው፡፡ በመሆኑም ደሙ ትኩስ አይደለም መማለዱ መስቀል ላይ ብቻ የቀረ እና ከትንሳኤ በኃላ አይሰራም ማለት የኪዳኑን ደም የመማለድ ስራ እንደማክፋፋት ነው። እንደ ቃሉም ያለቀና የተፈጸመ መስዋዕት ሲሆን የዘለአለም የማማለድ መስዋዕት ሆኖ በዘላለም መንፈስ የቀረበ ነው፡፡
ዕብ.9፡14
‹‹ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ስራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?››
በመሆኑም የመስቀሉ ስራ (የኢየሱስ ስም) አሁንም አይማልድም ብለው ኦርቶዶክሶች በማመናቸው በስሙ ውስጥ ያለውን የመማለድ ጉልበት እንዳይጠቀሙ በማድረግ በስሜ ለምኑ የሚለውን በመካድ የመስቀሉን መካከለኛነት አሁንም በስሙ እንደቀጠለ ባለመረዳት እንደማይሰራ በማሰብ በሌሎች ስም እንዲለምኑ አድርጓቸዋል፡፡ ይሄም የማስታረቅ አገልግሎት የሰጠንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ በመዘንጋት የማስታረቅ አገልግሎቱም የመስቀሉ ስራ(ስሙ) እንደሆነ ባለማስተዋል ሌላ የማስታረቅ አገልጋይ እና የማስታረቅ አገልግሎት(ስም) በመፈለግ ለመስቀሉ የማዳን ስራ ሌላ አማራጭ ይዘዋል፡፡ ቃሉ ያስተማረን ግን እግዚአብሔር ያዘጋጀልን የማስታረቅ አገልግሎት ለመዳንም ለሕይወትም የምንማጸነው በመስቀሉ ስራ (በስሙ) ነው፡፡ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስም በዚህ መልኩ ለሚቀርብ ጸሎት ብቻ የይቅር ባይነት ምላሽ ይሰጣሉ፡፡ የሚለመንበትን የመስቀሉን ስራ(ስሙን) በሌላ መተካት ደግሞ አምልኮ ነው፡፡


Copied from Seifu kiniso “Facebook “