🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ! ለመሆኑ አዲስ አመት ምን ማለት ነዉ? አመትስ እንዴት ነ | CEPHEUS TECH


እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!
ለመሆኑ አዲስ አመት ምን ማለት ነዉ? አመትስ እንዴት ነዉ ሚቆጠረዉ? ቀደምት አባቶቻችን በድሮ ጊዜ ሰአትና እለት የሚቀምሩት በካልኢት ፣ በኬክሮስ ፣ ሳልሲት ፣ ራብኢት ፣ ሀምሲትና ወዘተ ነበሩ።ስሌቱም፦
፩ (1) አለት ፦ ፷ (60) ኬክሮስ
፩ (1) ኬክሮስ ፦ ፷ (60) ካልኢት
፩ (1) ካልኢት ፦ ፷(60) ሣልሲት
፩ (1) ሣልሲት ፦ ፷ (60) ራብኢት
፩ (1) ራብኢት ፦ ፷ (60) ኀምሲት
፩ (1) ኀምሲት ፦ ፷ (60) ሳድሲት
(፩ (1) ካልኢት ፦ ፳፬ (24) ሴኮንድ ) ነው።
በዚህ የሰአትና ጊዜ መቀመሪያ ነዉ ከወራት በፊት የነበረዉን የፀሀይ ግርዶሽ ቀንና ሰአት በትክል ማስላት የተቻለዉ።
፩ (1) አመትም ስናሠላዉ ፫፻፷፬ (365) እለት ከ ፲፭ (15) ኬክሮስ ከ ፮ (6) ካልኢት ነው።
አሁን ያለንበት ወር (ጳጉሜ) ስሙ የመጣዉ ከግሪክ ሲሆን ትርጉሙም ፡ አመቱ ሲለካ የተረሳ ማለት ነው። ጳጉሜም በ 2300 ዓ.ም ፯ (7) ቀን ይኖራታል።
አሁን ይህ ሁሉ መረጃ ምን ይሰራል ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን ይህ ሁላ ሚያየዉ ትክክለኛ የሰአትና ስነከዋክብት ጥናት የተጀመረው አስከ ስድስተኛው ማይክሮ ሰከንድ የተቀመረዉ አዚዉ ሀገራችን በጥንት አባትና እናቶቻችን ነው ። (በጥናትም የዉጪዉ 2021/22 አቆጣጠር በ፯ (7) አመተ ስህተት አንዳለዉ ተረጋግጧል)

አሁን ደሞ እንቁጣጣሽ አዲስ አመት። ስሙ የመጣው (አንቁ ለጣጣሽ) ንጉስ ሰለሞን ለንግስት ሺባ ወደ ጄሩሳሌም ስትመጣ ባቀረበላት ስጦታ የተሠየመ ነዉ።ሰሙን ከዛ ያግኝ እንጂ ለኛ ዘመን ምንለዉጥበት ፣ አደይ አበባ የሚፈካበት ፣ ቃል ሚገባበት ፣ አቅድ ሚወጣበት ፣ ፀሀይ ሚወጣበትና በጋ ሚጀምርበት ነዉ። ይህ አመት የሰላም የፍቅር የጤና የመተሳሠብና የመረዳዳት ይሁንልን!
ሴፈስ ቴክ