🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​Kassmasse Negen Letizita Lyrics ነገን ለትዝታ አዲስ ስጦታ ለእኔ የሚሆን | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​Kassmasse
Negen Letizita Lyrics


ነገን ለትዝታ አዲስ ስጦታ
ለእኔ የሚሆን ሳታውቅ ሰምታ
እንደ ነብይ ቃል አብሮ እንደሚኖረው
ተከብሮ በሀገሩ እልፍ እንደሚያልፈው
እውነት ዛሬ ይንገስ ነገን ስለሚያውቅ
እውነት ዛሬ ይንገስ ነገን ስለሚያውቅ
አባቴ እናቴን ባያገኝ እኔ አልኖርም ነበር
አያቴም እሷን ባያገኝ እሱ አይኖርም ነበር
ፊቱንም እኔ ላድንቀው የማልም የነገን
እኔም ዛሬን ባላገኝ ነገ ላይኖር ነበር
ኋላው ጥላ ሆኖ ታሪክ አላመልጠው ነገር
ነገን ብቻ እያየው ልሮጥ ስንደረደር
አዋቂ ስሆን ልጅ ሳድግ ደግሞ አዋቂ
ትምህርት ከዛሬ አዎ እንደቀን ጠባቂ
የዕለት የዕለት እውቀት ቢገኝ እንደው ለነጠላ
ሀምሳ ሎሚ ከባድ ነው ከሆኑ ለብቻ
እንደሚታደል ነግሬ የእኔን ወሰድኩ ዛሬ
የድርሻውን ወስዶ ሁሉም ታደለች ሀገሬ
የእኔን የዛሬ ደግሞ ለእነሱ የነገ
ከአካፈሉኝ ከትናንት ለእኔም ዛሬ ሆነ
በነበር አልቀረም ድሮ አልቀረም ለዛሬ ሰው ሆኗል
ዛሬም አማረበት በቃ ታግዞ በትናንት
በል ያም ያውራ ለእሱ
እሱም ያውራ ለእሷ
እሷም ብትናገር
ምንም ሳትጨምር
የሰማውም ሰምቶ ላልሰማው ቢነግር
ቢያረገው ቀና ቢሆን ቁምነገር
ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር
ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር
ቢናገር ነው ሰው ሁሉም ይማከር
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ ሲነገር
ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ ሲነገር
ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር
እኔ ደግሞ ስናገር
ከሀገሬ ሰው ጋር ስማከር
ሀሳቤን ሁሉ ሰብስቤ
ሰላምታዬንም አቅርቤ
አንደበት ባለው ውብ ለዛ
በክፉ ነገ እንዳልወሳ
ግርማ ሞገሱን ከአንበሳ
ተኝቶ ውሎ ሲነሳ
ሳይጠየቅ ጥያቄ የሚያሳብ ለምላሹ
የማይቆጥር ውለታ እንዳይቆጥሩት እነሱ
ልጅ ሆኖ ሳለ ራሱ ምኞቱ ለታናሹ
ቸልተኛ ቅፅሉ በቅንፍም ታጋሹ
...ስር ንቅሳት
በእራሷ ቀለም ላድሳት
ያለሁት እዚው ከተማ
በውቧ በአዲስ አበባ
የሀገር ሰው ይሄን ሲሰማ
ድሮን ብሎ ቢለማ
ነገንም ደሞ ሲያልመው
አንድላይ ብንሆን ቢያስበው
ድሮም ድሮም ተዋግተው
አሁን ደሞ ተዋደው
ያኔም ለአንድ አላማ
አሁንም ይኸው አላማ
ፍቅር ፍቅር ተሞተ
ፍቅር ፍቅር ይሰማ
ፍቅር ፍቅር ተሞተ
ፍቅር ፍቅር ይሰማ
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (አምሮብን አዎ እንታይ) ሲነገር
ይነገር ይነገር (አምሮብን አዎ እንታይ) ሰላም ያለው ነገር
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (አምሮብን አዎ እንታይ) ሲነገር
ይነገር ይነገር (አምሮብን አዎ እንታይ) ሰላም ያለው ነገር
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (ፍቅር ፍቅር ተሞተ) ሲገር
ይነገር ይነገር (ፍቅር ፍቅር ይሰማ) ሰላም ያለው ነገር
በሀገሩ ሲወራ በጨዋታ (ፍቅር ፍቅር) ሲነገር (ፍቅር ፍቅር)
ይነገር ይነገር ሰላም ያለው ነገር


For More Join Us @cover_musics