Bizuayehu Demissie Meleyet Kifatu Lyrics ተስለሻል እንዴ ከዐይኔ ከመሀሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ ተስለሻል እንዴ ከዐይኔ ከመሀሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ የደመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ የደመናውን ጭስ ወደላይ አይኔ ተከትሎ በሃሳቡ ያይሻል ከባዶ ላይ ስሎ ከባዶ ላይ ስሎ የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው ቅር የሚል ደስታ የሚጣፍጥ ህመም ስሜት ነው ቅር የሚል ደስታ ሙሉው ጎደሎ ነው ትርጉሙ ትዝታ ትርጉሙ ትዝታ ከእኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራዉ ክሩ ከእኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራዉ ክሩ ይረበሻል ሆዴ ሲገረፍ ክራሩ ሲገረፍ ክራሩ ሲገረፍ ክራሩ አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት ስንቱን አሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳም አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም ሰማይ ደም ቢመስል ብትጠቁርም ጨረቃ ሳላይሽ አላድርም እኔ አልችልም በቃ አልችልም በቃ ደመናው ተቀዶ ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ አልችልም ለማደር ዓይኖችሽን ሳላይ አንቺን ሳላይ ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም ተስለሻል እንዴ ከዐይኔ ከመሀሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ ተስለሻል እንዴ ከዐይኔ ከመሀሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ አንቺ ብቻ እኮ ነሽ በሚታየኝ ሁሉ ስንቱን ጋራ ዞረሽ የኔ አለም ስንቱን ጋራ ዞሬ ስንቱን ጋራ ዞረሽ የኔ አለም ስንቱን ጋራ ዞሬ እንዴት እደአዲስ ሰዉ ታሚኛለሽ ዛሬ ታሚኛለሽ ዛሬ እስኪ ልጠይቀዉ ጥርስሽን ምን ይሆን ምክንያቱ እስኪ ልጠይቀዉ ጥርስሽን ምን ይሆን ምክንያቱ ፈገግ ብሎ ሸኘኝ ሲቆረጥ አንጀቱ ሲቆረጥ አንጀቱ ከእኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራዉ ክሩ ከእኔ አንጀት ይመስል ይገርማል የተሰራዉ ክሩ ይረበሻል ሆዴ ሲገረፍ ክራሩ ሲገረፍ ክራሩ ሲገረፍ ክራሩ አይታይሽም ወይ የኔ አበባ የልቤ ውስጥ እሳት ስንቱን አሳለፍኩት የኔ አለም አንቺን ላለመርሳት ሳድር ለብቻዬ የኔ አበባ ስወድቅ ስነሳም አስታውስሻለሁ የኔ አለም እኔ አንቺን አልረሳም ሰማይ ደም ቢመስል ብትጠቁርም ጨረቃ ሳላይሽ አላድርም እኔ አልችልም በቃ አልችልም በቃ ደመናው ተቀዶ ዶፍ ቢወርድ ከሰማይ አልችልም ለማደር ዓይኖችሽን ሳላይ አንቺን ሳላይ ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም ምን ጉድ ነዉ መለየት ክፋቱ ጨክኗል ተመዟል ከአፎቱ ሊለየን ሊያርቀን ቢነሳም አይችልም እኔ አንቺን አልረሳም Lyrics By @jo_ynwa For More Join Us @cover_musics 789 viewsJo, 06:25