Get Mystery Box with random crypto!

​​Adiss Leggesse Enjori Lyrics አንች የኢንጆሪ ፍሬ ማአዛሽ እያማረኝ... በ | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​Adiss Leggesse
Enjori Lyrics


አንች የኢንጆሪ ፍሬ ማአዛሽ እያማረኝ...

በሳማ በቆንጥር ባጋም በጋሬጣ
በእሾህ ተከበሻል በየት በኩል ልምጣ
የወንዙ ዳር መውጫው አዳልጦ እየጣለኝ
የጭቃ እሾሁ ነው ይበልጥ ያስቸገረኝ(2X)

አንች የኢንጆሪ ፍሬ ማአዛሽ እያማረኝ
በእሾህ ሀረግ በቅለሽ መውጫው አስቸገረኝ
እጅግ ያስደንቃል ውበት ጥፍጥናሽ
እሾህ ከበዛበት ምነው መብቀልሽ

ነብር አንበሳ ሞልቶ በጫካሽ በወንዙ
እባብ ነው ያስፈራኝ ባለ ትንፋሽ መርዙ
ከዘንዶው ካዞው ድንገት ከሚውጠው
እስስቷን ሳያት ነው የምደነግጠው

እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ(2X)

አንች የኢንጆሪ ፍሬ ማአዛሽ እያማረኝ
በእሾህ ሀረግ በቅለሽ መውጫው አስቸገረኝ
እጅግ ያስደንቃል ውበት ጥፍጥናሽ
እሾህ ከበዛበት ምነው መብቀልሽ

ከትልቁ ዛፍ ላይ ወጥተሽ ተጠምጥመሽ
ልመገብ አልቻልኩም ከጣፋጩ ፍሬሽ
ዋርካው ተገን ሁኖለ ሀሩሩ ጥላ
ሲያዩት ያስጎመጃል የፍሬሽ ዘለላ

እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ (2X)

እንዲህ ተጨንቄ ላገኝሽ ናፍቄ
አንቺ እየለመለምሽ እኔ እንዲህ ደርቄ
ያንቺ ቁመት ሲያድግ የኔው እያጠረ
አንጋጦ ማየቱ ልምዴ ሆኖ ቀረ (2X)


Lyrics By @abrshboy


Join Us For More @cover_musics