Get Mystery Box with random crypto!

​​Michael Belayneh Swedish Lyrics የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ እንደአለም ዳ | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​Michael Belayneh
Swedish Lyrics


የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንደአለም ዳርቻ እንደ ርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ

የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንደአለም ዳርቻ እንደ ርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ

እንደ ጽጌሬዳ እንደ አደይ አበባ
እንደከርቤ ብርቁ እንደ ሎሚ ሽታ
አበባ እንዳዬ ንብ እኔ እወድሻለሁ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው

ጡት እንዳዬ ህጻን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሺ ሂዎቴ ነው
አፈር መሬት ትቢያ እንደሚበላው
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው


የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንደአለም ዳርቻ እንደ ርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ
እኔ እወድሻለሁ እንደማታ ጀንበር
ያለም ቋንቋ አይበቃ ቢወራ ቢነገር
ብዙሺ ዘመናት እልፍ አሃላፍ ሌሊት
ሚሊዮን መሰለኝ ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ

አበባ እንዳዬ ንብ እኔ እወድሻለሁ
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሽ ልቅመሰው
እንደተወርዋሪ ኮከብ እማልጠግብሽ
ስወድሽ ስወድሽ ስወድሽ ስወድሽ

የሰማይ መሬቱ የባህር ስፋቱ
እንደአለም ዳርቻ እንደ ርቀቱ
አይኖችሽን ባይኔ ተዳክሜ እያየሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ
ስወድሽ ስወድሽ ዉዴ እወድሻለሁ


Lyrics By @jo_ynwa


For More Join Us @cover_musics