Tamrat Desta Marign Lyrics ጸጸት ታቅፌ ብቻዬን በናፍቆት ልቤ ሲጉላላ በረዶ ቤቴን አየሁት ጓዳው ከአሁኑ ሲላላ ልቤን እምቢ አለው ብዙ ነው ነውጤ ንጹህ ሰው ገፋህ እያለኝ ውስጤ የማዶ ስል ቂም ጣልኩት የአፋፉን ቅርቤን እያየሁ የደፍየደፉን አውቃለሁ በኔ ልብሽ ቢደማም ይቅር ለእግዚያቤር ማለት አይከፋም አይቁረጥ ልብሽ ይዞ ጥላቻ ማሪኝ የኔ አለም የዛሬን ብቻ ውበት ሸማዬ የክብር አርማዬ ማሪኝ አልሙትብሽ ምን አለኝ ሌላ ኩራቴ የምለው ልታመን ለፍቅርሽ እመኚኝ ፍቅሬ እምላለሁ ቃሌን በአምላክ ስም እሰጣለሁ አንችን ብቻ ስል ዘውትር ታምኜሽ እኖራለሁ አንችን ብቻ ስል (አንችን ብቻ) ዘውትር ታምኜሽ እኖራለሁ ሲገርፈኝ ባየሽ ሃዘን መከራ እያሳደደኝ የራሴው ስራ መች ህሊናየ እረፍ ይለኛል ባሰብኩሽ ቁጥር ያቃጥለኛል አውቃለሁ በኔ ልብሽ ቢደማም ይቅር ለእግዚያቤር ማለት አይከፋም አይቁረጥ ልብሽ ይዞ ጥላቻ ማሪኝ የኔ አለም የዛሬን ብቻ ውበት ሸማዬ የክብር አርማዬ ማሪኝ አልሙትብሽ ምን አለኝ ሌላ ኩራቴ የምለው ልታመን ለፍቅርሽ እመኚኝ ፍቅሬ እምላለሁ ቃሌን በአምላክ ስም እሰጣለሁ አንችን ብቻ ስል ዘውትር ታምኜሽ እኖራለሁ አንችን ብቻ ስል (አንችን ብቻ) ዘውትር ታምኜሽ እኖራለሁ Lyrics By @jo_ynwa For More Join Us @cover_musics 1.7K viewsJo, 07:35