Get Mystery Box with random crypto!

​​Mikiya Behailu Sebebe Lyrics ሰበቤ ሁን ሲልህ ባንተ አርጎ ሰበብ ሰበቤ ሁን | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​Mikiya Behailu
Sebebe Lyrics


ሰበቤ ሁን ሲልህ ባንተ አርጎ ሰበብ
ሰበቤ ሁን ሲልህ ባንተ አርጎ ሰበብ
ደስታዬን ከመረው እንደ ድንጋይ ክብ
አለም ሌላ መስሎኝ ብዙ ብዙ ስመኝ
አለም ሌላ መስሎኝ ብዙ ብዙ ስመኝ
መኖር ገና ጀመርኩ ከንፈርህ ሲስመኝ
ይቀኝልኝ ነፍስህ ለነፍሴ ዝማሬ
ይቀኝልኝ ነፍስህ ለነፍሴ ዝማሬ
እድሜዬን ለካሁት በፍቅርህ ጅማሬ
እድሜዬን ለካሁት በፍቅርህ ጅማሬ


ይመስለኝ ነበር ድሮ ፍቅር የገራገር
ይመስለኝ ነበር ድሮ ፍቅር የገራገር
አፌን ፈታሁ ገና ስላንተ ስናገር
ምን ቀረህ ልበልህ ፀጉሬንም ቆጥረሃል
ምን ቀረህ ልበልህ ፀጉሬንም ቆጥረሃል
ታሪኬን ገልብጠህ እንደ አዲስ ፈጥረሃል
ውዴ የኔ ነህ
ለነጠላ ነብሴ ተድላን የሞላህ
ፍቅሬ ላንተ ነው
እንደፀሃይ ጨረቃ ዘመኔን ላሰላው
ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን
ወረት እንደሰማይ ይራቀን
ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን
ወረት እንደሰማይ ይራቀን



ያሳለፍኩት ዘመን ካላንተ ፍቅር
ያሳለፍኩት ዘመን ካላንተ ፍቅር
ከዕድሜዬ ይሰረዝ ተቆርጦ ይቅር
ፍቅር ከሞላበት የትም ሁን ይመቻል
ፍቅር ከሞላበት የትም ሁን ይመቻል
ፍቅር የጎደለው አለም ይሰለቻል
የለመለመ ሰውነት ኧረ ያምራል ሰውነቴ
የለመለመ ሰውነት ኧረ ያምራል ሰውነቴ
ከንፈርህን ብጎርሰው አቅፌህ እንደናቴ
ከንፈርህን ብጎርሰው አቅፌህ እንደናቴ


አፍህ ከከንፈሬ ላፍታ ሳይነቀል
አፍህ ከከንፈሬ ላፍታ ሳይነቀል
ቀን እና ሌሊቱ አብሮ ይቀላቀላል
አለም ያሳየሀኝ ስንቱ ይቆጠራል
አለም ያሳየሀኝ ስንቱ ይቆጠራል
የፍቅር አባት ነህ ስሙ ባንተ ይጠራል
ውዴ የኔነህ
ለነጠላ ነብሴ ተድላን የሞላህ
ፍቅሬ ላንተ ነው
እንደፀሃይ ጨረቃ ዘመኔን ላሰላው
ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን
ወረት እንደሰማይ ይራቀን
ሁሌ ይሁንልን ብራ ቀን
ወረት እንደሰማይ ይራቀን
ወረት እንደሰማይ
ወረት እንደሰማይ
ወረት እንደሰማይ
ወረት እንደሰማይ
እህ ኦ ኦ ኦ ኦ
እህ እህ እህ እህ እህ
አህ እህ እህ እህ


Lyrics By @jo_ynwa


For More Join Us @cover_musics