Get Mystery Box with random crypto!

​​#RIP Alemayehu Eshetie Marign Biyeshalehu Lyrics አንዱን አካል | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​#RIP

Alemayehu Eshetie
Marign Biyeshalehu Lyrics


አንዱን አካል ፍቅር መለየት ገንጥሎት
አለሁ በግማሹ ደስታን ሃዘን ጥሎት
በደስታ ሃዘን በሳቅ ፈንታ ለቅሶ
የመረረው ፍቅር በእንባ ተለውሶ
ማሪኝ ብየሻለሁ
እሞትብሻለሁ

የአስታራቂ ያለህ እርዱኝ እባካችሁ
ብቸኛዋን ፍቅሬን አምጡልኝ ይዛችሁ
የአጋጣሚ ነገር ወይ ቀርቦዶሎ
ልቤ ከዳሽ እኮ በንዋይ ተታሎ
ማሪኝ ብየሻለሁ
እሞትብሻለሁ

ሰው ሁኖ ስህተትን የማይሰራ የለም
የአንድ ቀን ጥፋቴን ማሪኝ ተይ ግድ የለም
በደሌን እረስተሽ ማርኩህ በይኝ ፍቅሬ
በናፍቆት ሰንሰለት እንዳልኖር ታስሬ
ማሪኝ ብየሻለሁ
እሞትብሻለሁ

ጸጉርሽን ኮፍሽው በአልማዝ ማበጠሪያ
ይሁንልሽ ላንች የስምሽ መጠርያ
በስም መጠራቱ ላንች ያንስሻልና
የቆንጆዎች ንግስት እንድያው በደፈና
ቆዳዬ ተገፎ ይሁንልሽ ጫማ
ስጋዬም ይደገም ላንች ከተስማማ

ቆዳዬ ተገፎ ይሁንልሽ ጫማ
ስጋዬም ይደገም ላንች ከተስማማ
አጥንቴን ይብረደው እራቁቴን ልሂድ
ካንች የበለጠ አላገኝም ዘመድ
ማሪኝ ብየሻለሁ
እሞትብሻለሁ
ማሪኝ ብየሻለሁ
እሞትብሻለሁ


Lyrics By @jo_ynwa


For More Join Us @cover_musics