Get Mystery Box with random crypto!

​​Sami Dan Yemechershawa Seat Lyrics የመጨረሻዋ ሰአት የመጨረሻዋ ደቂቃ አ | Cover Musics & Lyrics♥️♥️♥️

​​Sami Dan
Yemechershawa Seat Lyrics


የመጨረሻዋ ሰአት የመጨረሻዋ ደቂቃ
አለፈች እኔን አስጨንቃ(እጅግ አስጨንቃ)
ከአይንሽ ላይ የአነበብኩት ተስፋ እምነትሽ ወድቆ
ያሁሉ ትግስትሽም አልቆ(ያ ትግስትሽም አልቆ)
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ያጣሁ እለት
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እንደ ሰው መቆም ያልቻልኩት


የመጨረሻዋ ሰአት የመጨረሻዋ ደቂቃ
አለፈች እኔን አስጨንቃ(እጅግ አስጨንቃ)
መርዶየን ስትነግሪኝ እኩል እኔም ነቃሁ
አይንሽ ሲገለጥ እጅግ ፈራሁ(ለካ ብቻዬን ነኝ ፈራሁ)
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ያጣሁ እለት
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እንደ ሰው መቆም ያልቻልኩት

ሁሌ ማይታረመው ይህ አንደበቴ
ቃላት የማይመርጠው ባዶ ጩሀቴ
አውቃለሁ ውዴ ስንቴ እንዳሳመመሽ እንደጎዳሽ
ከህሊናዬ ስመለስ ደግሞ ሳስበው እየዘገነነኝ
ግን ደግሞ የማያርመኝ እኮ ነኝ
ይገባኛል እኔ ብዙ ሌላ ቅጣት
ግን ባይሆን ይሻል ነበር አንችንስ ከኔ በማጣት
ስቃየም ሰርስሮ ከአጥንቴ እየገባ
የህሊናየ ቁስል አንች ላይ ያረግኩት ነገር ነው
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ያጣሁ እለት
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እንደ ሰው መቆም ያልቻልኩት
(ሆድዬ)
(ፍቅርሽን ያጣሁ እለት)
(ሆድዬ)
(ፍቅርሽን ያጣሁ እለት)

ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ሆድዬ
መውደድሽን ያጣሁ እለት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እኔማ የተሰበርኩት
ፍቅርሽን ያጣሁ እለት ያጣሁ እለት
ያኔ ነው እንደ ሰው መቆም ያልቻልኩት
(ሆድዬ)
(ፍቅርሽን ያጣሁ እለት)
(ሆድዬ)
(ፍቅርሽን ያጣሁ እለት)


Lyrics By @jo_ynwa


For More Join Us @cover_musics