Get Mystery Box with random crypto!

የሰማይ ጉባኤ

Logo of telegram channel dailyeyesus — የሰማይ ጉባኤ
Logo of telegram channel dailyeyesus — የሰማይ ጉባኤ
Channel address: @dailyeyesus
Categories: Uncategorized
Language: English
Subscribers: 3.53K
Description from channel

Wherefore God also hath highly exalted him, and given him a name which is above every name That at the name of Jesus every knee should bow, of things in heaven, and things in earth, and things under the earth.

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


The latest Messages

2022-08-06 00:13:20
በጣም ደስ እያለኝ ነው ይህንን ማስታወቂያ ወደ እናንተ የማደርሰው።ነሐሴ 15 እለተ እሁድ ከቀኑ 7:30 በራስ አምባ ሆቴል አዳራሽ ታላቅ የዝማሬ የምስጋና መርሃ ግብር አዘጋጅተናል።ኖላዊ ኄር የዝማሬ አልበም በእለቱ ይመረቃል ብዙ ዝማሬ ብዙ ምስጋና እናቀርባለን እባካችሁ ለሁሉም ሰው ሼር አድርጉልኝ ማንም ሰው እንዳይቀርብኝ
341 views አሳረፍኸኝ.. እ..ፎ..ይ.., 21:13
Open / Comment
2022-08-04 22:06:09

334 viewssolomon abubeker, 19:06
Open / Comment
2022-08-04 11:05:09

335 viewssolomon abubeker, 08:05
Open / Comment
2022-08-03 12:46:49

53 viewssolomon abubeker, 09:46
Open / Comment
2022-07-31 20:25:56 ማነው እንደኔ ማነው ?
ደጋግመው የሚሰሙትን አዲስ ዝማሬ እነሆ



179 viewssolomon abubeker, 17:25
Open / Comment
2022-07-24 14:02:20 1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
²⁴ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
በተሰቀለው አምኖ በመዳን ወራሽና ልጅ ከሆንን የተሰቀለውን ከፍ አድርገን ለመስበክ አናፍርም አዎን የተሰቀለው ኢየሱስን እንሰብካለን የተሰቀለው ኢየሱስ ያድናል እንላለን !! ጠቢባን ሲያዩት ሞኝነት አይሁዳዊም አይቶ የተሰናከለበትን እርሱ ለማዳን የሆነ የእግዚአብሔር ሀይልና ጥበብ ነው እንላለን ። የተሰቀለውን እንሰብካለን !!
@dailyeyesus
373 views አሳረፍኸኝ.. እ..ፎ..ይ.., edited  11:02
Open / Comment
2022-02-01 08:10:03 ነገር ግን እግዚአብሔር . . .

ቀድሞ ለእግዚአብሔር ከሚሆን ማንኛውም አይነት ፍቅር ሞተን ግራ ከሚያጋባው ዕውርነታችን ስር ተቀብረን ነበር (ኤፌሶን 2፡1) ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር . . . ።

ቀድሞ ለእራሳችን ክብር እና የራሳችን ጌታ ለመሆን ባለን ምኞት ተታልለን ነበር፤ ቀድሞ በአየር ላይ ሥልጣን ባለው አለቃ ሳናውቅ እንመራ ነበር (ኤፌሶን 2፡2) ነገር ግን እግዚአብሔር . . . ።

ቀድሞ በሥጋችን እና በአዕምሮአችን የስሜት ማዕበል እንግልት እየተነዳን ለሥጋችን ምኞት ተገዢዎች ነበርን (ኤፌሶን 2፡3) ነገር ግን እግዚአብሔር . . . ።

ቀድሞ የእግዚአብሔር ጠላቶች ነበርን (ሮሜ 5፡10) እንጠላው ነበር (ሮሜ 1፡30) የቁጣ ልጆች ነበርን። ነገር ግን እግዚአብሔር . . . ።

ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ ከአዕምሮ በላይ የሆነ ፍቅሩን ያሳይ ዘንድ ከእግዚአብሔር ተለይተን የሞተነውን፣ እግዚአብሔርን የማንፈልገውን፣ ከእግዚአብሔር ጋር የምንፎካከረውን፣ እግዚአብሔርን የምንጠላውን አጥንታቸው የደረቁ የቁጣ ልጆችን “በሕይወት ኑሩ” (ሕዝቅአል 37፡5) አለን።

ለእውነተኛ ውበት፣ ለእውነተኛ ክብር፣ ለእውነተኛ ተስፋ፣ ለእውነተኛ ደስታ እና ለእውነተኛ ፍስሐ ኑሩ አለን! ለእግዚአብሔር ኑሩ አለን (ገላትያ 2፡19) ፤ ለዘለዓለም ኑሩ አለን (ዮሐንስ 6፡58)!
1.4K views አሳረፍኸኝ.. እ...ፎ...ይ..., 05:10
Open / Comment
2021-10-14 08:36:48 በግ የሚጠፋው እረኛውን ሳይሆን ሌላኛውን በግ ሲከተል ነው፡፡ እውር እውርን ሊመራ እንደማይችል ሁሉ አንዱ በግ ሌላኛውን በግ ከአውሬ ሊያስመልጠው አይችልም፡፡
#tsedi
@dailyeyesus
1.5K views አሳረፍኸኝ.. እ...ፎ...ይ..., 05:36
Open / Comment
2021-10-13 18:34:33 እግዚአብሔር ስናጠፋ የታገሰን ለሃጢኣት የነበረው አሰራር ተቀይሮ ሳይሆን የታገሰን የልጁ የኢየሱስ ደም ምክንያት ሆኖ ነው።

@dailyeyesus
1.3K views አሳረፍኸኝ.. እ...ፎ...ይ..., edited  15:34
Open / Comment
2021-10-13 14:44:49 እግዚአብሔር ስለእርሱ ያለን መለኮታዊ እውቀት ስነ ምግባር እንዲሆንልን ይፈልጋል።
እግዚአብሔር ፍቅር ነው ስነ መለኮት ነው በፍቅር መመላለስ ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር ነው!!
@dailyeyesus
1.3K views አሳረፍኸኝ.. እ...ፎ...ይ..., 11:44
Open / Comment