🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በ2023ተኛው አገር አቀፍ የስራ አውደ ርዕይ / ከሪር ኤክስፖ ጥቅምት 7 እና 8 ላይ በአካል ሚሊ | Dereja

በ2023ተኛው አገር አቀፍ የስራ አውደ ርዕይ / ከሪር ኤክስፖ ጥቅምት 7 እና 8 ላይ በአካል ሚሊኒየም አዳራሽ ላይ ከመካሄዱ በተጨማሪ በቨርችዋል መንገድም ኢንትርኔትን በመጠቀም ይካሄዳል እናንተም እንድትሳትፉ ተጋብዛችኋል ።

ደረጃ ከ ስራ እና የክህሎት ሚኒስቴር በሚያገኘው ድጋፍና ከ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር እናንተን በመላው ኢትዮጵያ ላይ ከሚገኙ ቀጣሪዎች ጋር ለማገናኘት ይህንን አስደሳች ዝግጅት ይዞላችሁ መጥቷል ።

አዲስ አበባ ላይ ባትኖሩም እንኳን የስራ አውደ ርዕዩን በቨርችዋል መንገድ ኢንትርኔትን በመጠቀም ለመሳተፍ ትችላላችሁ ። ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ኦንላይን በምንሰጠው በቨርቹዋል መንገድ ስለሚካሄደው የስራ አውደ ርዕዩ ክፍል እና አውደ ርዕዩ የሚያስገኛቸው ዕድሎችን እንዴት በሚገባ መጠቀም እንደምትችሉ ለማስረዳት ያዘጋጀነውን ገለጻ እንድትካፈሉ እንጋብዛለን ።
ይህንን ገለጻ ከተካፈላችሁ በኋላ ጥቅምት 7 እና 8 ላይ በቨርቹዋል መንገድ ስለሚካሄደው የስራ አውደ ርዕዩን ክፍል ላይ በመሳተፍ የቅጥር ባለሙያዎችን አግኙ ፣ ስለተለያዩ የስራ ዕድሎች መረጃን አግኙ ፣ እንዲሁም ለወደፊት የሙያ እና የስራ ህይወታችሁ ጠቃሚ ምክሮችን ቅሰሙ ። እያዳያመልጣችሁ !

ቨርቹዋል ገለጻውን ለመሳተፍ በዚህ ሊንክ ተመዝገቡ ፡ https://forms.gle/iRcZXEb3HZL9R7HL7

ገለጻውን ለመሳተፍ የምትችሉበትን ሊንክ በቅርቡ እንልክላችኋልን !!

ስለ አገር አቀፍ የስራ አውደ ርዕዩ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ፣ ከዚህ በታች ባለው ስዕል ላይ የሚታየውን ኪው አር ኮድ ስካን በማድረግ ወይም የተቀመጠውን ሊንክ / መስፈንጠሪያ በመጫን የስራ አዉደ ርዕዩን በማስመልከት የተከፈተውን ግሩፕ ተቀላቀሉ ።

https://t.mederejaNationalCareerExpo2023