Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ አንዳንድ የሰሜንና ሰሜን ምዕራብ | DW Amharic

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጭጋጋማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ወደ አንዳንድ የሰሜንና ሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚያደርጋቸውን በረራዎች ከትናንት ከሰዓት በኋላ አንስቶ ማቋረጡን አስታወቀ። አየር መንገዱ ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር እና ላሊበላ የሚያደርጋቸውን በረራዎች የአየር ሁኔታው እስኪስተካከል ድረስ ማቋረጡን ያስታወቀው በይፋዊ የፌስ ቡክ ገፁ ነው። በኢትዮጵያ ሚትዮሮሎጂ አገልግሎት የትንበያ ባለሙያ የሆኑት አቶ ጥላሁን ውቤ ለአየር ሁኔታው ምክንያት ከሱዳን አካባቢ ያለው ከፍተኛ የሙቀት ግፊት የፈጠረው ችግር ከሱዳን የሚነሳ አቧራ አምና እና ካች አምናም ተመሳሳይ የበረራ መስተጓጎል ፈጥሮ እንደነበር ይታወሳል።