Get Mystery Box with random crypto!

ካርቱም-የሱዳን የዉኃ ሚንስትር ማስጠንቀቂያ የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያን በሰበብ-አስባቡ መጎነ | DW Amharic

ካርቱም-የሱዳን የዉኃ ሚንስትር ማስጠንቀቂያ

የሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮጵያን በሰበብ-አስባቡ መጎነታተላቸዉን እንደቀጠሉ ነዉ። የሱዳን ጦር ድንበር ተሻግሮ የኢትዮጵያን ግዛት ይዟል መባሉ አወዛግቦ ሳያበቃ ሠሞኑን፣ የካርቱም ባለስልጣናት የሕዳሴዉ ግድብ የዉኃ አሞላልን የአዲስ ማስጠነቀቂያ ሰበብ አድርገዉታል። የሱዳኑ የመስኖና የዉኃ ሚንስትር ትናንት እንዳሉት ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድን በተናጥል ዉኃ ከሞላች ለሱዳን ብሔራዊ ደሕንነት ቀጥተኛ ስጋት ትጭራለች። ሚንስትር ያሲር አባስ እንደሚሉት ኢትዮጵያ በመጪዉ ሐምሌ ግድቡን ከሞላች ሱዳን ከሁለት ግድቦችዋ የምታመነጨዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ይታወካል፤ የ20 ሚሊዮን ሱዳናዉያን ኑሮም ይቃወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈዉ ዓመት ክረምት ግድቡን መሙላት ጀመራለች። ግብፅና ሱዳን የኢትዮጵያን ርምጃ አልፈቀዱትም። ይሁንና የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በተደጋጋሚ እንዳሉት የዉኃ ሙሌቱ ይቀጥላል። ሮይተርስ ዜና አገልግሎት የሱዳኑን ሚንስትር ጠቅሶ እንደዘገበዉ የ3ቱን ሐገራት ዉዝግብ ለማስወገድ ዩናይትድ ስቴትስ፣የአዉሮጳ ሕብረት፣የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪቃ ሕብረት ሽምግልና እንዲገቡ ካርቱም ሐሳብ አቅርባለች።