Get Mystery Box with random crypto!

ሎክናዉ-ሕንድ-የበረዶ ክምር ተንዶ ብዙ አካባቢ አጥለቀለቀ ሰሜናዊ ሕንድ በሚገኙ ተራራዎች ላይ የ | DW Amharic

ሎክናዉ-ሕንድ-የበረዶ ክምር ተንዶ ብዙ አካባቢ አጥለቀለቀ

ሰሜናዊ ሕንድ በሚገኙ ተራራዎች ላይ የተከመረ በረዶ ተንዶ ሁለት የኤልክትሪክ ማመንጫ ግድቦችንና በርካታ መኖሪያ ቤቶችን ጠራርጎ ወሰደ። ዛሬ ሲነጋጋ የተናደዉ በረዶ ዝቅተኛ ቦታዎች የሚገኙ በርካታ አካባቢዎችን በጎርፋና ጭቃ አጥለቅልቋቸዋል። አደጋዉ የደረሰባት የኡታራካሐድ ግዛት አገረ-ገዢ ትሪቬንድራ ሲንጌሕ ራዋት እንዳሉት ጎርፉ ሰባት ሰዎች መግደሉ ተረጋግጧል። ሌሎች 125 ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም።