Get Mystery Box with random crypto!

ሞቃዲሾ-ቦምብ ፈንድቶ 12 የስለላ ሠራተኞች ተገደሉ ሶማሊያ ዉስጥ ዱሳማሬብ በተባለችዉ ከተማ አጠ | DW Amharic

ሞቃዲሾ-ቦምብ ፈንድቶ 12 የስለላ ሠራተኞች ተገደሉ

ሶማሊያ ዉስጥ ዱሳማሬብ በተባለችዉ ከተማ አጠገብ መንገድ ዳር የተቀበረ ፈንጂ 12 የመረጃ ወይም የስለላ ሠራተኞችን ገደለ። ዱሳማሬብ የሶማሊያ ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ነገ ሊደረግ ታቅዶ ስለነበረዉ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ለመነጋገር ተሰብስበዉባት የነበረች ከተማ ናት። ፖሊስ እንዳስታወቀዉ በአደጋዉ ከተገደሉት የስለላ ሠራተኞች መሐል አንዱ በከተማይቱ የሶማሊያ ብሔራዊ የመረጃና የፀጥታ መስሪያ ቤት ኃላፊ ነበሩ።ቦምቡን ያጠመደዉ የሶማሊያዉ አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አሸባብ መሆኑን ቡድኑ አምኗል። ታዛቢዎች እንደሚሉት የሶማሊያ ፖለቲከኞች የገጠሙትን ዉዝግብ አሸባብ እንደ ጥሩ አጋጣሚ ይመለከተዋል።