🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በጀርመን ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ግዛቶች የጣለው የበረዶ ግግር መደብኛ የመጏጏዣ እንቅስቃሴን አስተጏ | DW Amharic

በጀርመን ሰሜናዊ እና ምስራቃዊ ግዛቶች የጣለው የበረዶ ግግር መደብኛ የመጏጏዣ እንቅስቃሴን አስተጏጉሏል:: በሳምንቱ የስራ መጀመርያ ቀን ዛሬ ሰኞ ከማለዳ ጀምሮ በጣለው የበረዶ ውሽንፍር በእብዛኞቹ አካባቢዎች የባቡር እና የየብስ መጏጏዣዎች ተስተጏጉለዋል::
ትናንት እሁድ በጀርመን ኖርዝ ራየን ቬስትፋልያ ግዛት ብቻ 720 የአየር ሁኔታ ስጋት የስልክ ጥሪ መቀበሉን የግዛቲቱ ፖሊስ አስታውቋል:: በእለቱ ከአየር ጠባይ ጋር በተገናኘ ከ507 በላይ አደጋዎች ተመዝግበዋል:: በዚህም 37 መጠነኛ ጉዳቶች መድረሳቸው ተገልጿል::
በአውሮዻ እየበረታ የሄደው የክረምቱ የአየር ሁኔታ ከጀርመን ውጭ በቤልጅየም ኔዘርላንድስ እና እንግሊዝ በተመሳሳይ የመጏጏዣ እንቅስቃሴ ማስተጏጎሉ ተነግሯል:: በቀጣዮቹ ቀናት የበረዶ ውሽንፍሩ ተጠናክሮ በአብዛኞቹ የሰሜን አውሮዻ ሀገራት ሊወርድ እንደሚችል የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃዎች ያመለክታሉ::