Get Mystery Box with random crypto!

በጀርመን ባለፉት አስርተ ዓመታት ያልታየ የተባለለት የክረምት ወራት በተለይ በሰሜናዊ ጀርመን የባቡ | DW Amharic

በጀርመን ባለፉት አስርተ ዓመታት ያልታየ የተባለለት የክረምት ወራት በተለይ በሰሜናዊ ጀርመን የባቡር እና የተሽከርካሪን እንቅስቃሴን ገታ። በሰሜናዊ ጀርመን እንከ መካከለኛ ጀርመን በሚገኙ በተለያዩ ግዛቶች የሚጥለዉ የጥጥ ንድፍ የመሰለዉ በረዶ ለመጥረግ የመንገድ ትራንስፖርት ጉዳይ ሰራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ነዉ። ከበረዶዉ ሌላ ጎዳናዉ እጅግ አሸራተች መሆናቸዉ ብሎም የባቡር ሃዲዲች በበረዶ ክምር በመሞላታቸዉ እና ከፍተኛ ንፋስ በመኖሩ የመንገድ መጥረጉን ስራ እጅግ እንዳከበደዉ ተነግሮአል። የራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በበቦን ከተማ እጅግም በረዶ አይታይም።