🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዩናይትድ ስቴትስ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ወደ ነበራት የታዛቢነት ቦታዋ | DW Amharic

ዩናይትድ ስቴትስ በተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ወደ ነበራት የታዛቢነት ቦታዋ እንደምትመለስ አስታወቀች። በቀድሞዉ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በትራምፕ የስልጣን ዘመን አሜሪካ በጎርጎረሳዉያኑ 2018 ሐምሌ ወር ላይ ከመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የታዛቢነት ቦታዋን ለቃ መዉጣትዋ የሚታወስ ነዉ። ትራምፕ የመንግሥታቱን የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ምክር ቤትን ከሌሎች ጉዳዮች በተጨማሪ እስራኤልን በተደጋጋሚ በመተቸቱ ምክኒያት አድሏዊ አድርገው ቆጥረዉት ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ በዘረኝነት ዉንጀላ ምክንያቶች በምክር ቤቱ ዒላማ ስር ወድቃ ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ አሁን ወደ ተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ታዛቢነት ቦታ መመለስ ትራምፕ ከዓለም አቀፍ ግዴታዎች ለመላቀቅ ያሳለፉት ዉሳኔን በመቀልበስ በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር በጆ ባይደን የተወሰደ ተጨማሪ ርምጃ ነዉ።