🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የሶማልያ ተቃዋሚ መሪዎች ምርጫዉ መራዘሙን ይፋ ላደረጉት ለፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ -ፎ | DW Amharic

የሶማልያ ተቃዋሚ መሪዎች ምርጫዉ መራዘሙን ይፋ ላደረጉት ለፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ -ፎርማጆ የስልጣን እዉቅና እንደማይሰጡ ገለፁ። የሶማልያ መንግሥት ተቃዋሚዎች እዚህ ዉሳኔ ላይ የደረሱት ፎርማጆን ለመተካት ሊካሄድ የነበረዉን ምርጫ ምንም ፖለቲካዊ ስምምነት ሳይኖር ስልጣናቸዉን በገዛ ፈቃዳቸዉ በማራዘማቸዉ ነዉ። የሶማልያ የተቃዋሚዎች ጥምረት ፕሬዚዳንታዊ እጩ ፤ በሶማልያ የሽግግር ብሔራዊ መንግሥት እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል፤ ፕሬዚዳንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ ሕገ-መንግሥቱን እንዲያከብሩም አሳስበዋል። የሶማልያ ፕሬዝደንት መሃመድ አብዱላሂ መሐመድ ትናንት ለሃገሪቱ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ እንደነገሩት ተቀናቃኝ ፖለቲከኞች ባለመስማማታቸዉ ምርጫዉ አሁን ማካሄድ አልተቻለም ብለዉ ነበር። በሌላ በኩል ከሶማልያ መዲና መቃዲሾ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘዉ ድሻምሪብ ከተማ ለደረሰዉ ፍንዳታ ኧልሸባብ ኃላፊነትን ወስዶአል። ትናንት አካባቢዉ ላይ በደረሰዉ ፍንዳታ ቢያንስ 13 የሶማልያ የፀጥታ ኃይል አባላት መገደላቸዉ የሚታወስ ነዉ። ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ማካሄድ በነበረባት ወቅት ባለማካሄዷ የፖለቲካ ቀውስ ይገጥማታል የሚል ስጋት ተቀስቅሶአል።