Get Mystery Box with random crypto!

ደቡብ አፍሪቃ አስትራዜንካ ስተባለዉ የኮሮና መከላከያ ክትባት ዝርዝር መረጃ እስከምታገኝ ክትባቱን | DW Amharic

ደቡብ አፍሪቃ አስትራዜንካ ስተባለዉ የኮሮና መከላከያ ክትባት ዝርዝር መረጃ እስከምታገኝ ክትባቱን ጥቅም ላይ እንደማታዉል ገለፀች። ደቡብ አፍሪቃ ይህን የገለፀችዉ ብሪታንያ እና በስዊድን የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የሚመረተዉ አስትራዜንካ የኮnŀ መከላከያ ክትባት ምሁራን እና ተመራማሪዎች እንዴት ጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት ገና ምክር ላይ በመሆናቸዉ ነዉ ስትል ምክንያትዋን ሰጥታለች። ደቡብ አፍሪቃ ስለዚህ የኮሮና መከላከያ ክትባት ምሁራኑ አጠቃቀሙ ላይ ተማክረዉ ዉሳኔዉን እስኪሲጨርሱ ድረስ እንደምትጠብቅ ነዉ ያሳወቀችዉ። ከዚህ ቀደም ሲል የአስትራዚንካ የኮሮና ክትባት አምራች ኩባንያ፤ የመከላከያዉ ክትባት አይነት በደቡብ አፍሪቃ ለታየዉ የኮሮና ተኅዋሲ አይነት ጠንካራ የሆነ ፍቱነት እንደሌለዉ አሳዉቆ ነበር ተብሎአል።