Get Mystery Box with random crypto!

ቻድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሽብርተኞች ጥቃት ተጋላጭ የሆነውን የምዕራብ አፍሪቃ የሳህል ሃገራትን | DW Amharic

ቻድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለሽብርተኞች ጥቃት ተጋላጭ የሆነውን የምዕራብ አፍሪቃ የሳህል ሃገራትን እንዲደግፍ ጥሪ አቀረበች። ቻድ ጥሪውን ያቀረበችው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በበይነ መረብ ተሳታፊ የሆኑበት እና አምስት የሳህል ሃገራት የተገኙበት ውይይት በመዲናዋ በንጃሜና በተጀመረበት ወቅት ነው። ቻድ ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ማሊ፣ ሞሪታንያ እና ኒጀር እየመከሩ ባሉበት በዚሁ መድረክ የሳህል ቀጣና ሃገራት ድህነትን አምርረው በሚታገሉበት በዚህ ወቅት «ሽብርተኞች እንቅፋት ሆነውብናል» ሲሉ የቻዱ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ተናግረዋል። በዚህም ዓለም አቀፉ ማኅሕበረሰብ የአሸባሪዎችን የሽብር ምንጭ ለማድረቅ ለአካባቢው ሃገራት የሚያደርጉትን የልማት ገንዘብ ማሳደግ አለባቸው ብለዋል። የሳህል ሃገራት ስብሰባ ፈረንሳይ በቀጣናው ከአሸባሪዎች ጋር የሚደረገውን ውግያ ለማገዝ በአካባቢው ኃይሏን ማጠናከር ከጀመረች ከአንድ ዓመት በኋላ መካሄዱን የፈረንሳይ ዜና ምንጭ ዘገባ ያመለክታል። ፈረንሳይ በሳህል ቀጣና አገሮች ቀደም ሲል 4,500 የነበረውን የወታደሮቿን ቁጥር ወደ 5,100 ከፍ አድርጋለች።