Get Mystery Box with random crypto!

አርዕስተ ዜና -በትግራይ ክልል ከትናንት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መቋረጡ | DW Amharic

አርዕስተ ዜና

-በትግራይ ክልል ከትናንት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድርጅት ለዶይቼ ቬለ ገለፀ።የድርጅቱ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሞገስ መኮንን " የጁንታው ርዝራዥ " ባሏቸው ኃይሎች ትናንት ከቀትር በኋላ በተፈፀመ "ጥቃት" ከአላማጣ መሆኒ መቀሌ የተዘረጋው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር አገልግሎት አቋርጧል

-የሱዳን መንግስት በኢትዮጵያ የሐገሪቱን አምባሳደር ወደ ካርቱም ጠራ።ምክንያት ሁለቱ ሐገራት በድንበር ግዛት ይገባኛል ሰበብ ስለገጠሙት ዉዝግብ «ለመመካከር» ከመባሉ ሌላ ዝርዝሩ አልተነገረም።የሁለቱ ሐገራት ዉዝግብ እየተካረረ ነዉ።

-ኢትዮጵያን ጨምሮ ጦርነት፣ ግጭትና አለመረጋጋት በሚያብጣቸዉ ሐገራት ለሚኖረዉ ሕዝብ የኮቪድ 19ኝ ክትባት ለመስጠት ተኩስ እንዲቆም ብሪታንያ ጠየቀች።የብሪታንያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እንደሚሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ እንዲያቆሙ የሚጠይቅ ደንብ ማፅደቅ አለበት።ዜናዉን በድምፅ ለመስማት፣-https://p.dw.com/p/3pVBX