Get Mystery Box with random crypto!

አረብ ኤሚሬቶች ከአሰብ ወጣች የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አሰብ-ኤርትራ ላይ የገነባችዉን ዘመናይ የ | DW Amharic

አረብ ኤሚሬቶች ከአሰብ ወጣች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አሰብ-ኤርትራ ላይ የገነባችዉን ዘመናይ የጦር ሠፈር በከፊል ማፍረሷ ተዘገበ። ትንሺቱ የሰባት ተጫፋሪ ደሴቶች ስብስብ ኤሚሬትስ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር አብራ የየመን ሁቲዎችን ለመውጋት የሚረዳት የጦር ሠፈር አሰብ ውስጥ ገንብታ ነበር። እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ የተገነባው የጦር ሠፈር ዘመናይ ታንኮች፣ መድፎች፣ የጦር ጀልባዎች፣ ድሮኖችና ሌሎች ጦር መሣሪያዎችን የታጠቀ የራስዋ የአረብ ኤሚሬቶች፣ የየመንና የሱዳን ወታደሮች ሠፍረውበት ነበር። የአሜሪካው ዜና አገልግሎት አሶስየትድ ፕሬስ (AP) እንደዘገበው የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ለጦር ሠራዊቱና ለጦር መሣሪያ ማከማቻ ዘመናይ ወደብና ጠንካራ ምሽግ ገንብታለች። አዋራማውን አውሮፕላን ማረፊያም አድሳው ነበር። የጦር ሠፈሩን ከኤርትራ ለ30 ዓመት ተኮናትራው እንደነበርም ተዘግቧል። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በብዙ መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ያፈሰሰችበትን ጦር ሠፈር ማፈራረስ የጀመረችበትን ምክንያት በይፋ አላስታወቀችም። AP እንደዘገበው የኤርትራ ባለሥልጣናትም ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡት ላቀረበው ጥያቄ የሰጡት መልስ የለም። የፖለቲካና የወታደራዊ ጉዳይ አዋቂዎች እንደሚሉት ግን የአቡዳቢ ገዢዎች የአሰቡን ጦር ሠፈር ያፈራረሱት የመን ውስጥ የሚያደርጉትን ውጊያ ካቆሙ በኋላ ነው። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስትር ጂም ማቲያስ ባንድ ወቅት «ትንሿ ስፓርታ» (በተዋጊነታቸው የምትታወቀው የቀድሞ የግሪግ ከፊል-ግዛት) በማለት ያንቆለጳጳሷት ሐገር ገዢዎች በተራዘመው የየመን ጦርነት መቀጠል የሚያስችል አቅም እንደሌላቸው በመገንዘባቸው ነው። የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በፈራረሰው ጦር ሠፈር ተከማችቶ የነበረውን ጦር መሣሪያ በመርከብ ወደ ሐገራቸው እያጋዙ ነው።አሰብ ከየመን