Get Mystery Box with random crypto!

ባለፈው ጎርጎሮሳዊው 2020 ዓም በአውሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ተገን እንዲሰጣቸው ያመለከቱት ተሰ | DW Amharic

ባለፈው ጎርጎሮሳዊው 2020 ዓም በአውሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ተገን እንዲሰጣቸው ያመለከቱት ተሰዳጆች ቁጥር ከቀደመው ዓመት በ30 በመቶ ያነሰ እንደነበር ሕብረቱ አስታወቀ። ሕብረቱ እንዳለው የተገን ጠያቂዎች ቁጥር የቀነሰው በኮሮና ተኅዋሲ ወረርሽኝ ምክንያት ነው። ማልታ ዋና ከተማ ቫሌታ የሚገኘው የአውሮጳ የተገን አሰጣጥ ድጋፍ ሰጭ ቢሮ ዛሬ እንዳስታወቀው በጎርጎሮሳዊው 2020 በመላ አውሮጳ የተገን ማመልከቻ ያስገቡት ተሰዳጆች ቁጥር 461 ሺህ 300 ነበር። ይህም በቀደመው በ2019 ዓም ተገን ከጠየቁት 671 ሺህ 200 ጋር ሲነፃጸር በ30 በመቶ ያነሰ ነው። የ2020ው የተገን ጠያቂዎች ብዛት በአውሮጳ ከ2013 ወዲህ እጅግ ዝቀተኛው መሆኑ ነው የተነገረው። ድርጅቱ እንዳለው የተገን ጠያቂዎች ቁጥር የቀነሰበት ዋነኛው ምክንያት በኮሮና ሰበብ ሃገራት የጣሉት የጉዞ እገዳ ነው። የተገን ጠያቂዎች ቁጥር መቀነስም የተሰዳጆች ጉዳይ ከቀድሞ በተሻለ ፍጥነት እንዲታይ ረድቷል እንደ ድርጅቱ ።