Get Mystery Box with random crypto!

በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት ፖሊሲ ለውጥ እና መሻሻል ከተደረገ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ከሜክሲኮ | DW Amharic

በዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት ፖሊሲ ለውጥ እና መሻሻል ከተደረገ በኋላ የአሜሪካ መንግሥት ከሜክሲኮ ለሚመጡ የጥገኝነት ጠያቂዎች ድንበር እንዲያቋርጡ በድጋሚ መፈቀድ መጀመሩ ተመለከተ። አዲሱ የጥገኝነት ረቂቅ ውሳኔ ከዛሬ ዓርብ ጀምሮ ከሚክሲኮ የሚመጡ የጥገኝነት አመልካቾች ያቀረቡትን ማመልከቻ በፍርድ ቤት ለመከታተል ወደ አሜሪካ እንዲገቡና እንዲከታተሉ ይፈቅዳል። ውሳኔው ከመተላለፉ ቀደም ሲል ተገን ጠያቂዎቹ ተቀባይነት ስለማግኘት አለማግኘታቸው በሀገራቸው ሆነው እንዲከታተሉ የሚደነግግ ብቻ ነበር። አዲሱን የጥገኝነት ማሻሻያ ረቂቅ የዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራቶች ለፕሬዚዳንት ጆ ቢደን ኮንግረስ ውስጥ ለታሰበው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ረቂቅ በማስተዋወቃቸው ውሳኔው መተላለፉ ተመልክቷል። ውሳኔው ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ አሜሪካ ውስጥ ለሚኖሩ 11 ሚሊዮን ስደተኞች የመኖርያ ፈቃድን ለማግኘት መንገድ የሚዘረጋ እንደሆነ ተመልክቷል።