Get Mystery Box with random crypto!

በአፍሪቃ አህጉር በኮቪድ 19 በሽታ ባስከተለበት ሕመም የሞተው ሰው ቁጥር ከ 100 ሺህ መብለጡ ተ | DW Amharic

በአፍሪቃ አህጉር በኮቪድ 19 በሽታ ባስከተለበት ሕመም የሞተው ሰው ቁጥር ከ 100 ሺህ መብለጡ ተነገረ። በአፍሪቃ ሃገራት የኮሮና ተኅዋሲን ስርጭት ለመግታት የሚታየው ጥንቃቄ ቸልተኝነት ታይቷል ተብሏል ከገመትነው በላይ ለተኅዋሲው ተጋላጭ ሆነናል፤ ይህ በጣም የሚያሳዝን ነው ሲሉ የአፍሪቃ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ጆን ክኔጋሲጋ ለአሶሽየትድ ፕሬስ መናገራቸው ተመልክቶአል። «በአህጉሪቱ የሕክምና ባለሞያዎች ከባድ የሥራ ጫና ላይ ናቸው ሞትን የተለመደ እንዳናደርገው እፈራለሁ» ሲሉም የአፍሪቃ የበሽታዎች ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከል ዳይሬክተር ተናግረዋል። በአህጉሪቱ የኮሮናን ጉዳይ የሚከታተለው እና በአፍሪቃ ኅብረት የተቋቋመው ግብረ ኃይል ዛሬ እንዳስታወቀው፤ ሩስያ 300 ሚሊዮን ስፑትኒክ V የተባለውን የኮሮና መከላከያ ክትባት ለአህጉሪቱ ግንቦት ወር ዉስጥ እንደምትሰጥ አስታዉቃለች። ኅብረቱ ከዚህ ቀደም ሲል 270 ሚሊዮን የኮሮና መከላከያ ክትባትን ከአስትራዜንካ፣ ፋይዘር እና ጆንሰን ኤን ጆንሰን ከሚባለው አምራች ኩባንያ አግኝቶአል።