Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፖርላሜንታዊ የምርምር ትስስር ተቋማት ጋር በምርምር የተደገ | DW Amharic

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፖርላሜንታዊ የምርምር ትስስር ተቋማት ጋር በምርምር የተደገፉ ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ይጠቅማል የተባለለት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ። ምክር ቤቱ ከዚህ መግባባት ላይ የደረሰው ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እና የምርምር ተቋማት ጋር ከትናንት ጀምሮ አዲስ አበባ በሚገኘው በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሸ ሲያካሂድ በነበረው የመጀመሪያው ዓመታዊ የፓርላሜንታዊ የምክክር ጉባኤ ላይ ነው።
የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ዋና ፀሃፊ ዶክተር ምስራቅ መኮንን የሃገሪቱ ህጎች ሲፀድቁ በመረጃና በምርምር የተደገፉ እንዲሆኑ የምርምር ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው የምርምር ስራው በፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስኮች ዘላቂነት ያለው ስራ ለመስራት በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል። በስብሰባው የተካፈሉ ምሁራን« የመግባቢያ ሰነዱ ቀደም ብሎ ቢደርሰን የተሻለ ግብአት እናበረክት ነበር፤»« ተቋሙ እራሱን ችሎ ቢመራ የተሻለ ነው» የሚሉና ሌሎች አስተያየቶች ሰንዝረዋል ሲል በስፍራው የተገኘው ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዘግቧል። @dwamharicbot