Get Mystery Box with random crypto!

ከ 20 በላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸውን የጀርመን | DW Amharic

ከ 20 በላይ የደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንት ፅህፈት ቤት ሰራተኞች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸውን የጀርመን ዜና ምንጭ DPA ዘገበ። የፅህፈት ቤቱ ቃል አቀባይ አንቴኒ ዌክ አንቴኒ ለዜና ምንጩ በስልክ እንዳረጋገጡት በጠቅላላው ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የሚሰሩ 27 ሰዎች በትህዋሲው ተይዘው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ይገኛሉ። በሽታው የተረጋገጠባቸው ሰራተኞች በዋናነት የፕሬዚዳንቱ የጥበቃ ሰራተኞች፤ ምግብ አብሳዮች ፤ ሹፌሮች እና ራሳቸው ቃል አቀባዩም በተህዋሲው መያዛቸውን ገልጸዋል። «ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ ይገኛሉ» ያሉት ቃል አቀባያቸው ፕሬዚዳንቱ ከሰው ጋር ያላቸውን ግንኙነት በከፍተኛ መጠን እንደቀነሱ እና ከቤታቸው ሆነው እንደሚሰሩም ተናግረዋል። ደቡብ ሱዳን ውስጥ እስካሁን በይፋ 6,417 ሰዎች በኮሮና ተህዋሲ መያዛቸው የተመዘገበ ሲሆን 83 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ሞተዋል።