🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ታጣቂዎች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትጥቅ አስረከቡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በመተከል | DW Amharic

ታጣቂዎች ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትጥቅ አስረከቡ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በመተከል ዞን ውስጥ በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ውስጥ 72 የሚደርሱት የታጠቁ እና ሌሎች ድጋፍ ሲያደርጉላቸው የነበሩ 18 በድምሩ 90 የታጣቂ ቡድኑ አባላት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በሚል ትጥቃቸውን ለመንግስት ማስረከባቸውን ዐስታወቀ ። ታጣቂዎቹ በዞኑ ጉባ እና ዳንጉር ወረዳዎች ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ሲሆን፤ የሰላም ጥሪ ተቀብለው ተመለሱ የተባለው ትናንት ማምሻውን እንደሆነም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሩን ኡመር ለዶይቸ ቬለ (DW) ተናግረዋል ። በጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሥር የሚንቀሳቀሱ ናቸው ተብሏል ።

የመተከል ዞን ለረጅም ጊዜ በጊዜያዊ አስተዳደር ወይንም ኮማንድ ፖስት ሲተዳደር የቆየ ሲሆን፤ በታጣቂዎች እንቅስቃሴ እና የተለያዩ ጥቃቶች ምክንያት በዞኑ ብቻ ከ2 መቶ 60 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው ቆይተዋል ። በዞኑ በእጀባ ይሰጥ የነበረው የመጓጓዣ አገልግሎት በአሁኑ ወቅት መንገዶች ሙሉ በሙሉ ተከፍተው አገልግሎቱ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መመለሱንም ኮሚሽነሩ አስረድተዋል ።

የጉሙዝ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ ከክልሉ መንግስት ጋር ስምምነት ከተደረገ ጥቅምት 9 ቀን፣ 2015 ዓ.ም ወዲህ በድርጅቱ ስም ታጥቀው ይንቀሳቀሱ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችት ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀላቸውን ተናግረዋል ። የሰላም ጥሪውን የማይቀበሉ ታጣቂዎች ድርጅቱን እንደማይወክሉ እና ኃላፊነትም እንደማይስዱ ተናግረዋል ።

ዘገባ፦ ነጋሣ ደሳለኝ ከአሶሳ፤ ዶይቸ ቬለ (DW)
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid033uKsmRw2yCN9ABQqwEkoPyTD2Y19LyjBazRwareKymXUzEjkBo6LqWTV2Du6nkzql