🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በታንዛኒያው ድርድር ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተገለጠ የኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት | DW Amharic

በታንዛኒያው ድርድር ስምምነት ላይ አለመደረሱ ተገለጠ
የኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (OLA) ብሎ በሚጠራው መንግሥት «ሸኔ» በሚለው ታጣቂ ቡድን መካከል ታንዛኒያ ውስጥ ሲካሄድ የነበረው ድርድር «የመጀመሪያ ምእራፍ» ያለስምምነት መጠናቀቁ ተገለጸ ። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ በይፋዊ የማኅበራዊ መገናኛ አውታሩ ላይ ባወጣው ቁጥብ መግለጫ «ውይይቱ በአብዛኛው በአዎንታዊ መልኩ የተከናወነ ቢሆንም በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ግን በዚህኛው ምእራፍ ስምምነት ላይ ለመድረስ አልተቻለም» ብሏል ። አወንታዊ የተባሉትም ሆነ ስምምነት ያልተደረሰባቸው ጉዳዮች የትኞቹ እንደሆኑ ግን በግልጽ አልተቀመጠም ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት «የሰላም» ያለው ውይይት ታንዛኒያ ውስጥ መከናወኑን ከመግለጽ ባሻገር ግን ውይይቱ በማን እና በማን መካከል እንዲሁም በየትኞቹ ጉዳዮች መኪያሄዱን አልጠቀሰም ። ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን፦ (OLF-OLA press Release በሚል) ከሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ መጠሪያ «የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት» እንደሆነ እና ከዚህ ሌላ ማንኛውንም ስያሜ እንደማይቀበል በመግለጫው አስታውቆ ነበር ። በዛሬው መግለጫው መንግስት አንዳችም ስያሜ አልጠተቀመም ።
ይህ ጽሑፍ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በታጣቂ ቡድኑ በኩል ስለድርድሩ በይፋ የወጣ መረጃ የለም ። ለቡድኑ ቅርበት ያላቸው የተለያዩ የመረጃ ምንጮች ግን ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መስማማት አለመቻላቸውን ዘግበዋል ።
https://www.facebook.com/dw.amharic/posts/pfbid0245pnragAzXExxbYfcPZwDz7fteKzF8QKJYxdDxdP1Mnpe5AS9LHJtQeQHRrSMtfl