🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና በኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት | DW Amharic

የሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. ዐርዕስተ ዜና

በኢትዮጵያ መንግሥትና ራሱን “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ብሎ በሚጠራው ቡድን መካከል ዛንዚባር ታንዛኒያ ውስጥ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የሰላም ውይይት ዛሬ መጠናቀቁን የኢትዮጵያ መንግሥትና “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” አስታወቁ። ሆኖም የኢትዮጵያ መንግሥት እንዳለው በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ መስማማት አልቻሉም። የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ ጉዳዮች ባላቸው ላይ መስማማት አለመቻላቸውን ገልጿል።

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ቃል የገቡት የተኩስ አቁም እንዲጸና ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ዛሬም በተለያዩ የሱዳን ከተሞች ተኩስ ሲሰማ ነበር። ተፋላሚዎቹ ጀነራሎች ተኩስ ለማቆም የገቡትን ቃል አለመጠበቃቸው ዓለም አቀፍ ትችት አስከትሏል።

በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ፣ ጎርፍ ከ120 በላይ ሰዎችን ገደለ ። የሩዋንዳ ፕሬዝዳንት የፖል ካጋሜ ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው በሰሜንና ምዕራብ ሩዋንዳ ትናንት ለሊት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ቢያንስ 129 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል። የሟቾቹ ቁጥር ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4QrHk?maca=amh-RED-Telegram-dwcom