🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

አርዕስተ ዜና -የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስት ጦር መጠነ-ሰፊ ጥቃት ከፍ | DW Amharic

አርዕስተ ዜና
-የኦሮሞ ነፃ አዉጪ ሠራዊት (ኦነሠ) የኢትዮጵያ መንግስት ጦር መጠነ-ሰፊ ጥቃት ከፍቶብኛል በማለት ወቀሰ።የኢትዮጵያ መንግስት ኦነግ ሸኔ በሚል ስም በአሸባሪነት የፈረጀዉ አማፂ ቡድን እንደሚለዉ የመንግስት ጦር ጥቃት መክፈቱ ዛንዚባር-ታንዛኒያ ዉስጥ የተደረገዉን ድርድር የሚጥስ ነዉ።የኦነሠ ወቀሳ በገለልተኛ ወግን አልተረጋገጠም።


-የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይላት የገጠሙት ዉጊያ 25 ሚሊዮን የሚደርስ የሐገሪቱን ሕዝብ ለሰብአዊ ርዳታ ጠባቂነት ማጋለጡን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።ድርጅቱ እንደሚለዉ ችግረኛዉን ሕዝብ ለመርዳት ከ3 ቢሊዮን ዶላር በላይ ያስፈልገዋል።

-ሶሪያ ከ12 ዓመታት መገለል በኋላ የአረብ ሊግን ዳግም ልትቀየጥ ነዉ።የሶሪያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ዛሬ ካይሮ-ግብፅ ዉስጥ በተሰየመዉ የሊጉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ስብሰባ ላይ ተካፍለዋል።ፕሬዝደንት በሽር አል አሰድ ደግሞ የፊታችን አርብ ጂዳ-ሳዑዲ አረቢያ በሚሰየመዉ የሊጉ አባል ሐገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።ዜናዉ በዝርዝርና በድምፅ https://p.dw.com/p/4RWDe?maca=amh-RED-Telegram-dwcom@dwamharicbot