Get Mystery Box with random crypto!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት 801 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ። የሚኒስ | DW Amharic

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2016 ዓ.ም በጀት 801 ቢሊየን ብር እንዲሆን ውሳኔ አሳለፈ።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 21ኛ መደበኛ ስብሰባ "የሀገርን ደህንነት ከማስጠበቅ፣ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጐችን ከመርዳት፣ በሕግ ማስከበር ዘመቻ የወደሙ መሰረተ ልማቶች መልሶ ከማቋቋም፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና ዓላማዎች ከማሳካት አኳያ" ረቂቅ በጀቱ ተቃኝቶ የቀረበ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በጀቱ ለፌደራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች 369.6 ቢሊየን ብር፣ ለካፒታል ወጪዎች 203.9 ቢሊየን ብር ፣ ለክልሎች የሚሰጥ ድጋፍ 214.07 ቢሊየን ብር ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ 14 ቢሊየን ብር በጠቅላላው 801.65 ቢሊየን ብር ሆኖ ቀርቧል ተብሏል፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ረቂቅ ውሳኔውን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመራው መሆኑን የዘገበው ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ነው። አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot