Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በፓሪስ የዳይመንድ ሊግ የ300 ሜትር የመሰናክል ሩጫ አዲስ የዓለ | DW Amharic

ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ በፓሪስ የዳይመንድ ሊግ የ300 ሜትር የመሰናክል ሩጫ አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸነፈ። ለሜቻ ግርማ በቃጣራዊው ሳኢፍ ሳኤድ ሻሄን 7ደቂቃ 53ሰኮንድ 63 ማይክሮሰከንድ በሆነ ሰዓት ብራሰልስ ውስጥ በተመዘገበው እና ለ19 ዓመታት ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን 7 ደቂቃ ከ52 ሰከንድ 11 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ የርቀቱን ክብረ ወሰን ማሻሻል ችሏል። ውድድሩ ለረዥም አመታት በኬንያውያን የበላይነት ተይዞ መቆየቱ የኬንያውያን የባህል ስፖርት እስከ መባል ደርሶ እንደነበር ይታወሳል። ትናንት ምሽት በተመሳሳይ በተደረገው የሴቶች የ5000 ሜትር ውድድር ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፔይጎን አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በማስመዝገብ አሸናፊ ሆናለች። ኪፔይጎን በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን ክብረ ወሰን በአንድ ሰከንድ በማሻሻል ስታሸንፍ በርቀቱ ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት አግኝታ የነበረችው የርቀቱ የክብረ ወሰን ባለቤት ለተሰንበት ግደይ ሁለተኛ ወጥታለች። ፌይዝ ኪፔይጎን ክብረ ወሰን ስታሻሻል በሳምንት ጊዜ ውስጥ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው። የሁለት ጊዜ የዓለም ሻምፒዮናዋ የ29 ዓመቷ ፌይዝ ባለፈው ሳምንት በ1500 ሜትር የሩጫ ውድድር በኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ጸጋይ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን ክብረ ወሰን ማሻሻሏ አይዘነጋም።

https://p.dw.com/p/4SQSz??maca=amh-RED-Telegram-dwcom
አስተያየት ለመስጠት፣ ጥቆማ ለማድረስ ይኽን ቦት ይጠቀሙ @dwamharicbot