🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና | DW Amharic

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ
የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በደቡብ ክልል ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች በአንድ የጋራ ክልል ለመደራጀት ያካሄዱትን የህዝበ ውሳኔ ውጤት አጸደቀ ፡፡ በምክር ቤቱ የዛሬው 6ኛ የፓርላማ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ውብእሸት አየለ በዞኖቹና በልዩ ወረዳዎቹ የተካሄደውን የህዝበ ውሳኔ ውጤት በንባብ አቅርበዋልበህዝበ ውሳኔው 2 ሚሊየን 396 ሺህ መራጮች በጋራ ክልል መደራጀትን የደገፉ ሲሆን 120 ሺህ 268 ያህሉ ደግሞ የጋራ አደረጃጀቱን በመቃውም ድምፅ መስጠታቸውን ቦርዱ በሪፖርቱ አመልክቷል፡፡
በህዝበ ውሳኔው በአተገባበር ሂደት አጋጠሙ ያሏቸውን ችግሮችም በሪፖርታቸው የጠቀሱት ምክትል ሰብሳቢው “ በአንዳንድ አካባቢዎች የወረዳ አመራሮች በምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ ጫና ያደርጉ ነበር ፡፡ እንዲሁም ዕድሜያቸው ከአሥራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ነዋሪዎች ምርጫው ተሳትፈው ተገኝተዋል “ ብለዋል ፡፡
የቦርዱን የህዝበ ውሳኔ አፈጻጸም ያዳመጠው የፌዴሬሽን ምክር ቤት በበኩሉ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተወያየ በኋላ የህዝበ ውሳኔውን ውጤት በሙሉ ደምፅ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡ በዚህም መሠረት ላለፉት 30 ዓመታት ገደማ በደቡብ ክልል ሥር ሲተዳደሩ የቆዩት የዎላይታ ፣ የጋሞ ፣ የጎፋ ፤ የኮንሶ ፣ የደቡብ ኦሞ ፣ የጌዲኦ ዞኖችና አንዲሁም የአማሮ ፣ ቡርጂ ፣ ደራሼ ፣ አሌ እና ባስኬቶ ልዩ ወረዳዎች የፌዴራል ሪፐብሊኩ 12ኛ ክልል ሆነው እንዲደራጁ ምክር ቤቱ ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በእንጻሩ የሃድያ ፣ የከንባታ ጠንባሮ ፣ የሀላባ ፣ ሥልጤ ፣ የጉራጌ ዞኖችና እና የየም ልዩ ወረዳ ራሳቸውን መልሰው በማደራጀት በነባሩ ክልል እንዲቀጥሉ ሲል ምክር ቤቱ ወስኗል ፡፡
ዘገባ ፦ ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ፎቶ ፡ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት