Get Mystery Box with random crypto!

የሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና ኢትዮጵያ ያሰረቻቸውን ከፍተኛ የኦነግ አመራ | DW Amharic

የሰኞ ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና

ኢትዮጵያ ያሰረቻቸውን ከፍተኛ የኦነግ አመራር አባላት በአስቸኳይ እንድትለቅ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት Human Rights Watch በምህጻሩ HRW ጠየቀ። HRW የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዲፈቱ የጠየቀው ለሦስት ዓመታት በፖለቲካ ሚናቸው ምክንያት በኦሮምያ ፖሊስ በዘፈቀደ ተይዘው ታሰሩ ያላቸውን ሰባት የተቃዋሚው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ አመራሮችን ነው።

ተጨማሪ የ50 ብር ጉቦ አልሰጥም ያሉትን የ33 ዓመት ወጣት ሾፌር ፣የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የትራፊክ ፖሊስ አባላት ባለፈው አርብ ገደለዋል ሲሉ የሟች ቤተሰቦችና የስራ ባልደረቦቹ ለዶቼቬለ ተናገሩ። የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠሩት ሦስት የትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ አጥፍቶ ጠፊ በመቅዲሾ ወታደራዊ አካዳሚ ውስጥ ባፈነዳው ቦምብ ቢያንስ 13 ወታደሮች መገደላቸውንና 20 ደግሞ መቁሰላቸውን አንድ የዓይን ምስክር ተናገሩ። ለጥቃቱ ሃላፊነቱን የወሰደው አሸባብ ደግሞ የገደላቸው ወታደሮች ቁጥር 75፣የቆሰሉት ደግሞ 124 ናቸው ብሏል።

ሙሉውን ዜና ለማዳመጥ ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማገናኛ ይጫኑ
https://p.dw.com/p/4UKBK?maca=amh-RED-Telegram-dwcom