Get Mystery Box with random crypto!

የግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና ጠቅላይ ሚንስትር አህመድ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስ | DW Amharic

የግንቦት 25 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና ጠቅላይ ሚንስትር አህመድ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግስት እንደማይኖር አስታወቁ ።

የደቡብ ኮሪያው ፕሬዚዳንት ዮን ሱክ ዬኦል በርካታ የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች የሚሳተፉበትን ጉባኤ ጠሩ ። የፊታችን ማክሰኞ መዲናዋ ሴዑል የምታስተናግደው የኮሪያ አፍሪቃ ጉባኤ ሀገሪቱ ከአፍሪቃ ሃገራት ጋር በማዕድን ማውጣት ዘርፍ የነበራትን ትብብር ያጠናክራል ተብሏል።

በሰሞንኛው የደቡብ አፍሪቃ ምርጫ ሶስተኛ ከፍተኛ ድምጽ ያገኙት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ተፈጽሟል ያሉት «የምርጫ ጥሰት » ሳይመረመር አጠቃላይ ውጤት ይፋ እንዳይደረግ አሳሰቡ ።


አሜሪካ ፣ ግብጽ እና ቃጣር የጋዛው ዕልቂት እንዲያበቃ ያቀረቡትን የሰላም ሃሳብ እስራኤል እና ሐማስ እንዲቀበሉ አሳሰቡ ።

የሁቲ አማጽያን በቀይ ባሕር እና ህንድ ውቅያኖስ በስድስት መርከቦች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈጸማቸውን አስታወቁ ። የቀድሞው የኢራን ፕሬዚዳንት አህመዲንጃድ በድጋሚ ለፕሬዚዳነትነት ሊወዳደሩ ነው።

https://p.dw.com/p/4gYAu?maca=amh-RED-Telegram-dwcom