🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​ የጠፋው ሬሳ #ክፍል አስራ ዘጠኝ ...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩ | Emoji feelings🦋

​​ የጠፋው ሬሳ
#ክፍል አስራ ዘጠኝ

...ያ ሁካታ እና ጨዋታ በድጋሜ ፀጥ አለ በጣም ደነገጥኩኝ የምይዘው የምጨብጠው ጠፋኝ እንደምንም ተረጋግቼ አንድ ስርቻ ጋር ተሸጎጥኩ አሁንም ፀጥታው እንደቀጠለ ነው ይመስለኛል ጆሯቸውን ቀስረው በድጋሜ የኔን ድምፅ እየጠበቁ ነው ማንም ከተቀመጠበት የተነሳ የለም...በዚህ ሰዓት ከተደበኩበት ቦታ ቀስ ብዬ በጥንቃቄ ተነሳሁ ልወጣ በሩ አካባቢ ስደርስ ሰውዬውም ሊወጣ ነው መሰለኝ ከወንበሩ ተነሳ ወዲያውኑ ወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ ይባስ ብሎ ሰውዬው ሊወጣ ብሎ ወደሗላ መለስ አለ የጠረጠረው እንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝ "በቃ ከዚህ በሗላ ማምለጥና መትረፍ አይታሰብም" ብዬ ለራሴ ነግሬ ጭንቅላቴን ጉልበቴ መሀል አስገብቼ የሚሆነውን መጠባበቅ ጀመርኩ እዛው በቃረቀርኩበት ደቂቃዎች ተቆጠሩ ከዛም እንደምንም ድፍረቴን ሰብስቤ ፍራቻዬን ተቋቁሜ ከአንገቴ ቀና ብዬ ስመለከት ሰውዬው በሩ ጋር አልነበረም በጣም ግራ ገባኝ ሲራመድ እንኳን ኮቴ አልተሰማኝም ነበር አሁን የባሰ ጭንቅ ሆነብኝ ሰውዬው ከየት እንደሚመጣ ለመገመትም ከበደኝ ቀስ ብዬ ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ከተደበኩበት ተነስቼ ቅድም ውስጥ ያለውን ነገር እመለከትበት ወደነበረው የመጋረጃው ሽንቁር ተጠጋሁ ሁለቱ ሴቶች እንደነበሩት ናቸው በአርምሞ ሆነው የሮቤልን አካል ይመገባሉ ቀና ብለው እንኳን አይተያዩም ነበር ግን ከዛ አረመኔ ሰውዬ የተሻለ የተስተካከለ የፊት አቀማመጥ እና ጤናማነት ይታይባቸዋል በድንገት አይኔ ተወርውሮ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለው ሁለት የህፃናት ፎቶ ላይ አርፎ ቀረ "እነዚህ ብላቴናዎች ማን ሊሆን ይችላሉ" ብዬም አሰብኩ በድጋሜ በዛች ሽንቁር ዙሪያ ገባውን መቃኘት ጀመርኩ በድጋሜ አንድ ፎቶ ተመለከትኩ አንዲት መልከ መልካም እናት በጨርቅ የተጠቀለለ ልጅ አቅፋ ከሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ቆማ ያሳያል በእርግጥም ሆስፒታሉን አውቀዋለሁ አሁን ያለንበት ቦታ ነው በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር "ህፃን ታቅፋ ፎቶ ላይ ያለችው ሴት ማን ልትሆን ትችላለች" ብዬ ራሴን ጠየኩ ዳሩ መላሽ ባላገኝም በድጋሜ አይኔን ወርወር አድርጌ ሌላ ነገር ማየቴን ቀጠልኩ ፎቶዎቹ በአጠቃላይ ጥቁርና ነጭ ቀለመሸ ያላቸው ናቸው...አይኔን ግድግዳው ላይ ሳንከባልል አንድ መልከ ሸጋ ብላቴ ያለበትን ፎቶ ተመለከትኩ ማን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ቢከብድም ገዳዩ ሰውዬ ይሆን እንዴ ብዬም አሰብኩ ግን የማውቀውን የፊቱን ገፅታ እና አቀማመጡን ሳስበው ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችል ደመደምኩ ግን እነዚ የፎቶ ስብስቦች ያለ ምክንያት እንዳልተሰደሩም ተገንዝቤያለሁ በድንገት በዕድሜ ጠና ያለችው ሴትዮ ተነስታ ስመለከት ወደነበረው መልከ መልካሙ ብላቴና ፎቶ ጋር ጠጋ ብላ በእጆቿ እየዳበሰች በስስት አይን እየተመለከተች ድምፅ ሳታሰማ የእንባዋን ጎርፍ በጉንጯ ላይ ታወርደዋለች ከዛው ሌላኛዋ ሴት ተነስታ ከሗላ በኩል እቅፍ አርጋ የፊቷን የግራ ክፍል ጀርባዋ ላይ አስደግፋ ዝም ብላ አብራት ቆመች ከደቂቃዎች በሗላም ሴትየዋ ማልቀሷን አቆመች ወደነበሩበትም ተመለሱ ግን አሁንም ፊቷ አልተፈታም ነበር ሁለት እጆቿን በእልህ ጨብጣ ከንፈሯን ነክሳ በፍጥነት መተንፈስ ጀመረች ምን ሆነች ሳይባል በድንገት ተነስታ የክፍሉን ዕቃ አመሰችው በዚ ጊዜ ሰውዬው ድምፅ ሰምቶ ሊመጣ ይችላል ብዬወደነበርኩበት ስርቻ ተመለስኩ አሁን ንግግር ጀምረዋል "እባክሽ እባክሽ ተይ ተረጋጊ" ትላለች በዕድሜ አነስ የምትለዋ "ልጄን ልጄን ልጄን በሉብኝ አንድዬን የአይኔን ማረፊያ የፈጣሪዬን ስጦታ በሉብኝ" እያለች ድምፇን ከፍ አርጋ አምርራ ታለቅሳለች "ራስሽን አትጉጂ እባክሽን ተረጋጊ መድሃኒትሽን መውሰድ አለብሽ እንዲ መሆን የለብሽም የባሰ ታስጨንቂዋለሽ" አለቻት "ማነው ሚጨነቀው" ብዬ ወዲያውኑ ራሴን ጠየኩ "ሴትየዋ ልጄን በሉብኝ ብላ ነው ምታለቅሰው በሉብኝ ማለት ደግሞ ገደሉት ይመስለኛል እና ስለየትኛው ሰው እና ስለየትኛው ልጅ ነው እንደዚ ካየሽ ይጨነቃል" የምትለው ብዬ ከራሴ ንግግር ጀመርኩ የዚህ ቤተሰብ ውስብስብ ታሪክ ይበልጥ ዘልቄ እንዳውቃቸው አጓጓኝ ግን መሞትም እንዳለ አልዘነጋሁትም በድጋሜ ከተደበኩበት ተነስቼ ወደመጋረጃው ሽንቁር አመራሁ አሁን ፀጥታው ተመልሶ ነግሷል ሴትዬዋ መሬት ላይ ተኝታለች በዕድሜ አነስ የምትለው ደግሞ በተኛችበት ፀጉሯን እየደባበሰች ታፅናናታለች የሴትየዋ ጉዳት ከባድ እንደነበር መገመት ቀላል ነው ልጇን ምንም ያርጉት ምንም በብዙ ተጎድታለች ሰው ነችና አሳዘነችኝ አነስ የምትለዋ ሴት መድሃኒቱን እንድትውጥ አድርጋ አረጋጋቻት እዛው ቆሜ በመጋረጃው ሽንቁር እየተመለከትኩኝ ሳለ በድንገት በሩ ተከፈተ ስዞር.............

............ይቀጥላል..........

ቀጣዩን#ክፍል ሀያ እንዲቀጥል
ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ



Join&share

ማንበብ ባህላችን ይሁን