Get Mystery Box with random crypto!

#UPDATE #ፍትህ_ለፌቨን! ግድያ የተፈፀመው እዚሁ ሀዋሳ ነው። ኃይሌ ሪዞርት አካባቢ አሳ | @እንደኔ እይታ.....

#UPDATE

#ፍትህ_ለፌቨን!

ግድያ የተፈፀመው እዚሁ ሀዋሳ ነው።

ኃይሌ ሪዞርት አካባቢ አሳ መሸጫ ማህበር እንዳጣራሁት መረጃ ግለሰቡ በተደጋጋሚ ሴቶችን በጀልባ ላዝናናሽ በማለት ወደ ውስጥ አርቆ ይዞ በመሄድ ሰው መድረስ የማይችልበትና ጮኸው እንኳ እንደማያመልጡ የሚያውቁበት ቦታ ላይ ሲደርሱ ለፆታዊ ትንኮሳ ጥያቄና ከዚያ ከፍ ሲልም ወደ ማስገደድ ይመጣል።

የግለሰቡን ማስፈራራት እና፣ ጮኸው እንኳ ሰው የማይደርስበት ቦታ ላይ እንዳሉ ሲያውቁ ያሎት አማራጭ ከግለሰቡ የሚቀርብልዎትን ክፉ ሀሳብ መቀበል አለበለዚያም ዘሎ ሀይቅ ውስጥ መግባት ሊሆን ነው።

ይህች ታዳጊ ግን ይህ ዕጣ ደርሷታል! ሞትን ፈርተው በግድ ወንጀል ተፈፅሞባቸው ምንም እንዳልተፈጠረ የሄዱ እህቶችን ቤት ይቁጠራቸው።

የሀዋሳ ከተማ ወንጀል ክትትልና ምርመራ ይህንን ጉዳይ አጣርቶ ተገቢውን የህግ ቅጣት ወንጀል ፈፃሚውን እንዲቀጣ ስል ድምፄን አሰማለሁ።

በታዳጊዋ አሰቃቂ ሞት ሀዘን ለደረሰባችሁ ቤተሰቦችና ጓደኘኞቿ በሙሉ መፅናናትን እመኛለሁ!!

Via #EFREM