🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የግራፊክስ ዲዛይን ክህሎቶችን መማር ለምትፈልጉ አራት ጠቃሚ ድረ ገፆች ----------------- | 𝖊-𝖘𝖆𝖋𝖊

የግራፊክስ ዲዛይን ክህሎቶችን መማር ለምትፈልጉ
አራት ጠቃሚ ድረ ገፆች
--------------------------------------------------------

የምስሎችንም ይሁን የግራፊክስ ዲዛይኖችን በሚፈለገው ደረጃ አስውቦ ለመስራት አያሌ የቴክኒክ እና የልምድ ክህሎቶችን ጠንቅቆ ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ አንዱ እንኳን ጎሎ ቢገኝ በምንሰራው የግራፊክስ ዲዛይን ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ሊያሳድር ይችላል፡፡ ታዲያ ጀማሪ የግራፊክስ ዲዛይነሮች እነዚህን ቀላል የማይባሉ የቴክኒክ እና የልምድ ክህሎቶችን በሚገባ ለማወቅ እንዲያስችላቸው እነዚህን ጠቃሚ ድረገፆች ቢጎበኙ መልካም ነው፡፡

1. Canva
ይህ የድረ ገፅ ምንጭ በግራፊክስ ዲዛይን ዙሪያ የሚሰሩ ማንኛቸውንም ስራዎች የሚያጠቃልል ቀዳሚ ድረ ገፅ ሲሆን ብዙዎችም ለአጠቃቀም የሚመርጡት ነው፡፡ ድረ ገፁ የኦንላይን ፕሮግራሞችን በኢንተርኔት ላይ የሚያሰራጭ ከመሆኑ በተጨማሪም አስገራሚ የስእል እና የግራፊክስ አይነቶችን በበይነገፁ (interface) ላይ በማከል ተጠቃሚዎች የራሳቸውን ማሻሻያ እንዲያደርጉና የተለያዩ ቴክኒኮችን በቀላሉ እንዲማሩ የሚያስችል ነው፡፡
2. Stencil
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገፆች ላይ የተለያዩ ስእሎችን ለመፍጠር እና ለማስዋብ የሚፈልጉ ከሆነ ይህ የድረ ገፅ ምንጭ ትልቅ እገዛ ሊያደርግሎት ይችላል፡፡ በተለይም ልዩ የግራፊክስ ዲዛይኖችን በማህበራዊ ሚዲያ ለማጋራት እንዲችሉና ለተለያዩ የንግድ እንቅስቃሴዎች የሚያስፈልጉ የሎጎና የማስታወቂያ ተግባራትን እንዲያከናውኑ የሚያስችል ማእቀፍ በድረ ገፁ ላይ በመካተቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ ዲዛይነር ለመሆን ያስችሎታል፡፡
3. Crello
ይህ ድረ ገፅ ከ33 በላይ የቴምፕሌት (templates) አሰራሮችን ከ 10 ሺ የግራፊክስ አይነቶችን ጋር አጣምሮ የያዘ ሲሆን በአይነቱ ልዩ የሆነ የግራፊክስ ዲዛይን ለመስራት የሚፈልጉ ተጠቃሚዎች የመጨረሻውን የቴምፕሌት ደረጃ የሚያገኙበትም ድረ ገፅ ነው፡፡ በዚህ ድረ ገፅ ላይ የሚሰሩ ግራፊክሶች አብዛኛውን ግዜ አስደማሚ ይዘት ያላቸው ሲሆን ዲዛይናቸውም የላቀ ቴክኒክ የሚጠቀም ነው፡፡
4 Piktochart
ይህ የድረ ገፅ አይነት ከ600 በላይ የሆኑ የፕሮፌሽናል ይዘት ያላቸው የኢንፎግራፊክስ (infographics) ቴምፕሌቶችን በማረ አቀራረብ ለተጠቃሚዎቹ የሚያደርስ ሲሆን የተዋበ የኢንፎግራፊክስ ዲዛይን ለመስራት የሚመኙ ሰዎች ምኞታቸውን የሚያሳኩበትም ነው፡፡ ድረ ገፁ በቀላሉ የተለያዩ ቴክኒኮችን ለመማር የሚያስችል ፕላትፎርም በመዘርጋቱ ማንኛውንም የኢንፎግራፊክስ አይነቶች ለመለማመድ ብዙም ከባድ አይደለም፡፡
ምንጭ፡ Tech Viral


@esafeSoftwareSolution
@esafeSoftwareSolution