Get Mystery Box with random crypto!

መና ገልማ አባ ገዳ (Mana Galma Abbaa Gadaa) ====================== ር | ancient history of oromoo and oromia

መና ገልማ አባ ገዳ
(Mana Galma Abbaa Gadaa)
======================
ርቱዕ ጀማ፥ ብጹዕ ጀማ
ለካ አንተነህ...
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ያደ ኦሮሞ ሻማ
ዋቃ ገዲኒ፥ ነማ ኦሊኒ
ሱማ፥ አከ ሱማ
የተሰኘው፥ እንደአክሱማ
የተባልከው፥ ፍጹም ጀማ
ለካ አንተነህ......
-
አገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
አባ ሰርዳ፥ አባ ገዳ
አባ ፈርድ፥ ነበልባሉ
እም ቅድመ-ኦሪት፥ ባህሉ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
ቃ’ሉ’፥ የማይቀለበስ ቃሉ
ለካ አንተነህ........
-
ሴኧ’ት፥ አርካ
ኦ’ግ ገዳ፥ የአድባር ዋርካ
ያ’ዴ እናቴ፥ ያዴ እሴቴ
ያ’ዴ አቴቴ፥ ያዴ እቴቴ
ያቴ ኦራ፥ የኩሽ ነዶ
አባ ቦኩ፥ አከሚዶ
ባናትህ ጸሃይ፥ ከለቻ
የምትጠልቅ፥ አንተ ብቻ
የካም ኢደ ኢዶ ምድር
ተነባቢ፥ አስር ምስጢር
አባ ወሮ፥ አባ ወራ
አባ ባሮ፥ አባ በራ
አባ ካሮ፥ አባ ከራ
የጅቡቲም፥ ጀበጂሾ
የመቅዲሾም፥ መቀዲሾ
የነሙቴሳ፥ ከምበልኣ
እንደ ባሮ፥ ከምበልኣ
መነ..ደላ፥ አከ መንደላ
መቀ..ደላ፥ አከ መቅደላ
የፉላኒ፥ ካኖ ደላ
የምትሰኝ፥ የምታሰኝ
የጎና ቤት፥ አባ ከራ
የላሊ ቤት፥ ላሊ በራ
የከረዩ፥ አባ ከራ
በጎፈሬህ፥ ስሪት ላባ
አዶ አዶዬ፥ ውብ ቀዘባ
አዳ የከለቻ ተሸላሚ
የአዱ ግንባር፥ ተቀዳሚ
የአዲስ ዘመን፥ መጸው አደይ
አዳ አዱኛን፥ እልል እሰይ
የምታሰኝ፥ የምትሰኝ
አዱ አዱኛ፥ አባ ቢሌ
የአካ ኪሌ፥ የአባቢሌ
ለካ አንተነህ........
-
ገዳ ገዳም፥ የአለም ሰላም
ገዳ ቢሉሱማ ሳቃ
ፈካ ጉራቻ፥ አካ ዋቃ
የጻህፍት አምላኩ አኒ
ያለበሰህ ድርብ ከኒ
የጥቁር ፥ ፈርኦን ልሳን
የአዴ ኣዳ፥ ፀሃይ ብርሃን
የአዱሊስ፥ አዱኛ ኪዳን
አባ ገዳ፥ አባ በኣል
የቅድመ አክሱማዊት ቃል
የአስርቱ በሮች፥ መሰላል
የማለዳ ንጋት፥ ፀዳል
የኦሩስ፥ ኦሪሳ ተምሳል
ለካ አንተነህ...........
-
ኣገ ኦጋ፥ ጂገ ሎጋ
ያኢ ቢያ፥ አባ ቃሉ
የማይቀለበስ፥ ቃሉ
ርቱዕ፥ ጀማ
የተባልከው፥ አገሱማ
እንደ አክሱማ
ያደ ኦሮሞ፥ ሻማ
አባ ገዳ፥ ኢልመ ገልማ
ለካ አንተነህ........
( ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ቀዌሳ 1964)

Text and pictures :Social media


#ancient_history_of_oromoo