Get Mystery Box with random crypto!

#ancient_history_of_oromo .............ኤለሞ ቂልጡ............ . ወ | ancient history of oromoo and oromia

#ancient_history_of_oromo .............ኤለሞ ቂልጡ............
.
ወላጆቹ ያወጡለት ስም ሀሰን ኢብራሂም ኡመር ይባላል፡፡ትውልዱ ሀረርጌ ውስጥ ወተር ቡልሎ ከምትባለው መንደር በ1936 ነው፡፡የልጅነት ታሪኩ እምብዛም ባይታወቅም
እስከ1956 በትውልድ መንደሩ የእስልምና ትምህርትን የተማረ ሲሆን በ20አመቱ ወደ ድሬዳዋ በመሄድ ትውልዳቸው የመን
ከሆኑ የየመን ነጋዴዎች የጨርቃጨርቅ መደብር ስራ አግኝቶ በታማኝነት ለአጭር ጊዜ እንደሰራ የወጣቱን መልካም ባህሪ ያስተዋሉት ቀጣሪዎቹ ወደ የመን ይዘውት ሄደው ኑሮውን በኤደን መሰረተ፡፡
.
ያ..ወጣት በአጭር ጊዜ በንግዱ አለም የተዋጣለት ሁኖ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሀገሩ ልጆች በሱ ቤት ሰብሰብ ብለው ስለ
"ኦሮሙማ" ሲያወሩ እምብዛም ትኩረት ባይሰጠውም በኤደን ያለው የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽህፈት ቤት ቀልብ ግን ሀሰን
ኢብራሂም እና በቤቱ የሚሰባሰቡ የኦሮሞ ተወላጆች ላይ ትኩረቱን አጠናክሯል፡፡
.
. በ1967ለኢትዮጵያ መንግስት ይሰልል የነበረ የሀረሪ ተወላጅ ሰው አዴን ይሄድና ዕቃ በዱቤ ተቀብሎት ከሱ ጋር ወደ ፊንፊኔ በመሄድ ክፍያውን እንዲቀበል ይህን ወጣት አግባባው። ወጣቱ ምንም አላቅማማም ተስማምቶ አብሮት ወደ ፊንፊኔ ተጓዘ።
.
ፊንፊኔ እንደደረሰም ወድያውኑ በቁጥጥር ስር ውሎ በፀረ ኢትዮጵያ አሸባሪዎች እንቅስቃሴ አባልነት ተከሰሰ። በእስር ቤቱም እጅግ አሰቃቂ አካላዊና ስነ ልቦናዊ ስቃይ ደረሰበት።ይህ
አጋጣሚ የዚህን ወጣት ህይወት ቀየረው፡፡ኦሮሞነት ወንጀል መሆኑን፡፡
.
.ወገኖቹ ገንዘብ በማዋጣት ለእስር ቤቱ ሃላፊ ከፍ ያለ ገንዘብ በመስጠት ከእስር ቤቱ አስለቀቁት። ወጣቱ በእስር ቤቱ በነበረው ሁኔታ አመለካከቱን ብቻ አልነበረም የቀየረው ስሙንም ጭምር እንጂ፡፡ወላጆቹ ያወጡለትን ስም በመተው ለራሱ "ኤለሞ ቂልጡ "በማለት ለጓደኞቹ ሲያስተዋውቃቸው በደስታ
ነበር የተቀበሉት፡፡
.
ኤሌሞ በኦሮሞነት ስለታሰረ በማንነቱ እንዲያምን አደረገው።ወድያውኑም በወቅቱ
በመጫና ቱለማ ራስ አገዝ ማህበር አመካኝነት በሀገሪቱ ፈንጥቆ የነበረውን የኦሮሞ ብሄራዊ ንቅናቄን ተቀላቀለ።
.ብዙም ሳይቆይ ግን የመጫእናቱለማ አባላት ወደ እስር ሲጋዙ ያ የኦሮሙማው ቀንዲል መቶ አለቃ ማሞ መዘምርን አንገት ንጉሱ ለገመድ ሲዳርጉ የነጻነት ፋኖውን ጀነራል ታደሰ ብሩን
ለግዞት መላካቸውን ያየው ኤለሞ ልቡ እንዳገነገነ በዝምታ አልተቀመጠም፡፡ትግሉ በመሳሪያ እና መሳሪያ ብቻ መሆኑን አምኗል፡፡
.
በ1968 ኤሌሞ በምስጥር ወደ ሶማሊያ (ሞቃድሾ)በመሄድ የኦሮሞ ብሄራዊ አቀንቃኞች ስብሰባ ላይ ተካፍሎ የኦሮሞ
ብሄራዊነት አጀንዳ ማስተዋወቅ የሚል ተልዕኮ
ተሰጠው። ወደ አዴን ተመለሰና የኦሮሞ ማህበረሰብ ህብረትን መሰርቶ የአዴን ከተማ አስተዳደሪን በማሳመን የኦሮሞ ፖለቲካ
ቢሮን ከፈተ።ከተለያዩ ሀገራት፣ ከፍልስጤም ነጻነት ንቅናቄ እና የኤርትራ ነፃ አውጭ ግንባር ድጋፍን ማፈላለግ ጀመረ።በኢራቅ መንግስት እርዳታም የ7 ወር ወታደራዊ ስልጠና ፕሮግራም ለኦሮሞ ነጻነት ተዋጊዎች በማዘጋጀት ጠንካራ የሽምቅ ተዋጊዎችን አፈራ።እነዚህንም ሀይሎች በጓደኛው
አብዱልከሪም ሀጂ ኢብራሂም (ጃራ አባ ገዳ) መሪነት በሰሜን ሶማሊያ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ላከ።
.
በ1973 መጀመሪያ ላይም ኤሌሞ በፊንፊኔ የኦሮሞ ምስጥራዊ ንቅናቄ መሪዎች ስብሰባ ላይ እንዲሳተፍ ተጋበዘ። በስብሰባውም የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ለመጀመሪያ ግዜ ተመሰረተ። ኤሌሞ ቂልጡም በኢትዮጵያ
መንግስት ላይ የትጥቅ ትግልን የመክፈት ሃላፊነት ተሰጠው።ከስብሰባውም በኋላ የትጥቅ ትግሉን ለመጀመር ከትግል ጓደኛው ሁንዴ ታቂ ጋር ወደ ገለምሶ አቀኑ።
.
በ1974ሚያዚያ ወር ከጥቂት ተከታዮቹ ጋር በጨርጨር አውራጃ (የአሁኑ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን) ውስጥ ከሚገኘው የጉባቆርቻ ወረዳ የትጥቅ ትግሉን ጀመረ፡፡ በወቅቱ በገለምሶ
ከተማ ውስጥ በግዞት ላይ ከሚገኙት ጄኔራል ታደሰ ብሩ እና አሕመድ ተቂ ከሚባለው ታዋቂ ነጋዴ ጋር የግንኙነት መስመር መሰረተ፡፡ እነዚህ ሶስት አርበኞች ህዝቡን በፖለቲካ እያነቁ
አደራጁ፡፡ ወጣቶችም ወደ ንቅናቄው መቀላቀል ጀመሩ፡፡በሀምሌ ወር 1974በተደረገ አንድ ኦፕሬሽን በኤሌሞ ቂልጡ የሚመራው
ጦር ጄኔራል ታደሰ ብሩን በውድቅት ሌሊት
ከገለምሶ አስወጥቶ ወደ ሸዋ አሻገረ፡፡ በዚህም የተነሳ በወቅቱ ስልጣኑን ከኃይለ ሥላሴ መንግሥት በመረከብ ላይ በነበረው
የደርግ መንግሥት ላይ ከፍተኛ መደናገጥ ተፈጠረ፡፡ ስለዚህ ደርጎች ቡድኑን አድኖ የሚያጠፋ ሁለት ሻምበል ጦር ወደ
ገለምሶ ላኩ፡፡ ይህ የደርግ አዳኝ ጦር በኤሌሞ ቂልጡ የሚመራውን የኦሮሞ ሽምቅ ተዋጊዎች ቡድን ለሁለት ወራትያህል ሲያሳድድ ከረመ፡፡ የነ ኤሌሞ ቡድንም የነበረውን አነስተኛ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት የደርግ ጦርን ፊት ለፊት ሳይጋፈጥ አነስተኛ ጥቃቶችን እየከፈተ መሸሹን ቀጠለ::
.
ነሐሴ 30/1974ግን የቁርጥ ቀን ሆነ፡፡
ሁለቱ ሀይሎች “ጢሮ”በተሰኘች ቦታ ፊት ለፊት ተገጣጠሙ፡፡ የኤሌሞ ጦር የውጊያ ፍላጎት ያልነበረው ቢሆንም የደርግ ጦር የቀድሞ ማጥቃት እርምጃ ወሰደ፡፡ ከኤሌሞ ጦር ሁለት
ሰዎችንም ገደለ፡፡ የሁለቱ ሰዎች ሞት ኤሌሞ ቂልጡን በከፍተኛ ቁጭት ውስጥ ከተተው፡፡
በተለይ ከሟቾቹ አንዱ አሕመድ ተቂ (ሁንዴ) የተባለው የኤሌሞ ተወዳጅ ጓደኛ መሆኑ ገና ከተመሰረተ አጭር ጊዜ የሆነው የኦሮሞ ነጻነት ሽምቅ ተዋጊዎችን ለበቀል እንዲነሳሱ
አደረጋቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ኤሌሞ ዘጠኝ ተከታዮቹን ብቻ ይዞ ከደርጉ ሀይል ጋር ተጋጠመ፡፡ሁለቱ ሀይሎች ቀኑን ሙሉ ሲዋጉ
ዋሉ፡፡ ከአንድ መቶ ሀምሳ በላይ ያለውን የደርግ ሀይል ተቋቁመው ሲመክቱ የነበሩት በኤለሞ የሚመሩት የኦሮሞ ነጻነት ሀይሎች እየተመናመነ ሄደ በመጨረሻም በፍልስጥኤም ነጻ አውጪ ድርጅት ስር
የሰለጠነው እና የደርጉን ጦር ገትሮት የዋለው ጀግና በመጨረሻ ተከበበ፡፡
.
እጅ መስጠትን ለቀጣዩ ሰራዊት ሊያስተምር እንደማይሻ እያወቀ በሆዱ ላይ ቆስሎ የነበረ በመሆኑ እርሱን የከበቡት የደርግ ሰዎች
መጥተው እንዲወስዱት ነገራቸው፡፡ ከባቢዎቹም አምስት ወታደሮችን ወደ ስፍራው ላኩ፡፡ ሆኖም ወታደሮቹ ከቦታው ደርሰው ኤሌሞን ለመውሰድ ሲሞክሩ ያልታሰበ አደጋ
ገጠማቸው፡፡ ኤሌሞ ያሰናዳው የእጅ ቦንብ የሁሉንም ጥቃቅን አካል ሽቅብ ሲያጎነው ኤሌሞ ቂልጡም በዚያች ቅጽበት ተሰዋ፡፡
በዚያ ውጊያ ላይ ከኤሌሞ ቂልጡ ጋ የተሰዉት ጓዶቹ
-አሕመድ ተቂ (ሁንዴ)
-ኮሎኔል ማሕዲ አሕመድ
- ሼኽ ጀማል እና
-ሱለይማን ይባላሉ፡፡
.
@etbisahusen