Get Mystery Box with random crypto!

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ለኢንጅነሪንግ እና ለአየር ሀይል ቴክኒሻንነት ለሚማሩ የወጣ የቅጥር ማስ | Ethionline jobs

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ለኢንጅነሪንግ እና ለአየር ሀይል ቴክኒሻንነት ለሚማሩ የወጣ የቅጥር ማስታወቂያ ፡፡

1. አጠቃላይ የምልምላ መስፈርት

1.1. የኢ.ፌ.ዴ.ሪን ህገ-መንግስት የተቀበሉ፡፡
1.2. በህዝቦች ሉአላዊነትና አንድነት የሚያምን እና በፅናት ለማገልገል
ሙሉ ፍቃደኛ የሆኑ፡፡
1.3. ከማንኛውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወገንተኝነት ነፃ የሆኑ፡፡
1.4. ከአሁን በፊት የመከላከያ ፣ የፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል አባል
ያልነበሩ፡፡
1.5. በወንጀል ይሁን በፍትሀብሄር ተከሰው የፍርድ ቤት ክርክር
የሌለባቸው፡፡
1.6. ኢትዮጵያዊ የሆኑ፡፡
1.7. የተስተካከለ ቁመና ያላቸው የእግር፣ እጅ፣ አንገት፣ የወገብ መሰበር ችግር የሌለባቸው፡፡
1.8. የሰውነት ህዋሳቶች የአይን፣ የጆሮ፣ የጥርስ፣ የከንፈር እና የአፍንጫ ችግር የሌለባቸው፡፡
1.9. ከውስጥ ደዌ በሽታዎች ከቲቪ፣ ከሚጠል በሽታ፣ ከስኳር፣ ከደም ግፊት፣ ከኪንታሮት እና ከእንቅርት ነፃ የሆኑ፡፡
1.10. በህብረተሰቡ ተቀባይነት ያለውና ከተለያዩ አጉል ሱሶች የራቁ፡፡
1.11. ከላይ ለተጠቀሱት ፖለቲካዊ መስፈርቶች ከቀበሌ መስተዳድርና ከፖሊስ የፅሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
1.12. መከላከያ በወታደር ኢንጅነርነት በሚያሰማራው ቦታ ሁሉ በታማኝነት ለመስራት ፍቃደኛ የሆኑ፡፡
1.13. ለኢንጅነሪንግ ተመልማዮች ለተማሩት ሙያ እጥፍ ለማገልገል ፍቃደኛ የሆኑ፡፡
1.14. መብትና ግዴታቸውን አውቀው የሚሠሩ ትዳር ያልመሰረቱና ልጅ ያልወለዱ።
1.15. ከላይ ለተጠቀሱት የምልመላ መስፈርቶች ከቀበሌ ፣ ከወረዳና ከፖሊስ የጽሁፍ ማሰረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. አካላዊ ብቃት

2.1.ቁመት ለወንድ 1 ነጥብ 60 ሴንቲ ሜትር ፣ ለሴት 1 ነጥብ 55 ሴንቲ ሜትር እና ከዚያ በላይ፡፡
2.2.ክብደት ለወንድ ከ50 እስከ 70 ኪሎ ግራም ፣ ለሴት ከ45 እስከ 60 ኪሎ ግራም፡፡
2.3.ዕድሜ ከ 18-24 ዓመት፡፡
2.4.የጤንነት ምርመራ ለማድረግ ፍቃደኛ የሆኑና የጤና ምርመራውን ያለፉ፡፡

3. የትምህርት ሁኔታ፦

• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ የሆኑ፡፡
• የ8ኛ እና የ10ኛ ክፍል ኦርጅናል ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
• የ10ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በእንግሊዘኛ ፣ በሂሳብ ፣
በፊዝክስና በኬሚስትሪ C እና ከዚያ በላይ ያላቸው፡፡
• ከ9 እስከ 10ኛ እና ከ11ኛ እስከ 12ኛ የተማሩበት የትምህርት ውጤት
ወይም ትራንስክሪፕት ዋናውን ማቀረብ የሚችሉ፡፡
• በ2010 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ቢያንስ
ለወንድ 352 ለሴት 330 ነጥብ ያላቸው፡፡
• በ2011 ዓ.ም የከፍተኛ መግቢያ ፈተና ወስደው በአራት የትምህርት
አይነቶች ማለትም በሂሳብ ፣ እንግሊዘኛ ፣ ፊዚክስና አፕቲቲዩድ
ቢያንስ ለወንድ 176 ለሴት 166 ያላቸው፡፡
• ለ2012 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ቢያንስ
ለወንድ 380 ለሴት 368 ነጥብ ያላቸው፡፡
• በተለያዩ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ለመደበኛ የቅድመ ምረቃ
ፕሮግራሞች/በሳይንስ እና በኢንጅነሪንግ የትምህርት መስክ ትምህርት
በመከታተል ላይ ለሚገኙ፣
• የ2012 ዓ.ም ጨምሮ የየሴሚስተሩን የትምህርት ውጤት ሪፖርት
ማቅረብ የሚችሉ፡፡
• በሳይንስ በፊዚክስ በኬሚስትሪ በሂሳብ እና በአፕላይድ ሳይንስ
የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ድግሪ ለ2012 /2013 ዓ.ም
የተመረቀ/ች/ የቴምፕራሪ ድግሪ ስቱደንት ኮፒ
እና ኦፊሻል ትራንስክሪብት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
• በአዲሱ የትምህርት ፖሊሲ በ2011/በ2012 ዓ.ም በቴክኒክና ሙያ ደረጃ
4 በተፈጥሮ ሳይንስ የተመረቁ እና የደረጃ 4 ብቃት ማረጋገጫ ወይም
ሲ.ኦ.ሲ (COC) ያላቸው
• በስራ ፈጠራ በልዩ ችሎታ እና በትምህርት የላቀ ውጤት ያላቸው
ይበረታታሉ።
• ሴት ተመልማዮች ይበረታታሉ።

4. የምዝገባ ቦታና ጊዜ

4.1. የምዝገባ ቦታ፣
• ለአዲስ አበባ እና ለአካባቢው ተመዝጋቢዎች በመከላከያ መኮንኖች
ክበብ ፊት ለፊት ባለው ሚሊተሪ ፖሊስ በር በመግባት መረጃና ማስረጃ ቢሮ አካባቢ ሲሆን፣
• ለክልል ተመዝጋቢዎች በየአካባቢያችሁ ባሉ የወረዳ፣የዞን
አስተዳደርና ፀጥታ ወይም የሚሊሻ ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣

4.2. የምዝገባ ጊዜ
• የምዝገባ ጊዜው ከግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ሰኔ 12 ቀን 2013 ዓ/ ም ድረስ ይሆናል።
• በክልልና በዞን ከግንቦት 26 ቀን 2013 ዓ/ም እስከ ሰኔ 10 ቀን 2013 ዓ.ም ምዝገባ ይጠናቀቃል፡፡

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር