🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን በአይነቱ ልዮ የሆነ ለተወዳዳሪዎች እና ተመ | Exotic Ethiopian Cars

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሞተር ስፖርት አሶሴሽን በአይነቱ ልዮ የሆነ ለተወዳዳሪዎች እና ተመልካቾች ምቹና ማራኪ ኮምፓክት ራሊ የመኪና ውድድር ለ ሁለተኛ ጊዜ አዘጋጅቶ እንድትሳተፋ ይጋብዛል::

በውድድሩ ላይ መሳተፍ ለምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ምዝገባ

- ከመጋቢት 30/ 2013 ዓ.ም(April 8/2021) እስከ ሚያዝያ 9/2013 ዓ.ም (April 17/ 2021) ድረስ ያለቅጣት!

- ከሚያዝያ 10/ 2013 ዓ.ም (April 18 /2021) እስከ ሚያዝያ 13/2013 ዓ.ም (April 21/2021)በቅጣት

መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የውድድሩ ጊዜ ሰሌዳ እንደሚከተለው ይሆናል:-


የተወዳዳሪዎች ገለፃ (Briefing) :- ሚያዚያ 14/ 2013(April 22 /2021)
ፍተሻ (Scrutiny) :- ሚያዚያ 16 /2013 (April 24 /2021)
የውድድር ቀን :- እሁድ ሚያዚያ 17 /2013 (April 25 /2021)

*ውጤት ማሳወቂያ ቀን- ሚያዚያ 26/2013 (May 4/2021)

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

አንድ ተወዳዳሪ Copilot (አጋር አሽከርካሪ) ይዞ መምጣት ይኖርበታል
1. የሁለቱም የታደሰ ህጋዊ መንጃ ፈቃድ
2. 2×2 ጉርድ ፎቶ(pilot 2 & copilot 2) ድምር4
3. ሊብሬ ወይም :-
ሀ. የሞተር ቁጥር
ለ. የቻንሲ ቁጥር
ሐ. የታርጋ ቁጥር
መ. መኪናው የተሰራበት ዘመን
ሠ. የመኪናው ስሪት (ሞዴል)
ረ. መኪናው የተሰራበት ሀገር

4. መመዝገቢያ ያለቅጣት 2,500 ብር (በቅጣት 3,500 ብር)
5. መታወቂያ / ከሌለ ትክክለኛ አድራሻ የሚገልፅ ህጋዊ ማስረጃ
6. እድሜ
7. ሜዲካል ሰርተፊኬት pilot & copilot (በ2013 የውድድር ዓመት የተወዳደራችሁ ተወዳዳሪዎችን አይመለከትም)
8. አባልነት ክፍያ የ2013 ዓ/ም ያልከፈላችሁ ነባር ተወዳዳሪዎች 120 ብር
ለአዲስ ተወዳዳሪዎች አባልነት ክፍያ 170 ብር
9. እድሜው ከ 21አመት በታች የሆነ ተወዳዳሪ ወላጅ ወይም ማናጀር ሀላፊነት በመዉሠድ መፈረም ይኖርበታል

ምዝገባ ቦታ ሜክሲኮ ፖፖላሬ አካባቢ በሚገኘው መብራቱ ጋራዥ መታችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን

ማሳሰቢያ!

-የምዝገባ ፎርም በምትሞሉበት ጊዜ pilot & copilot ሁለቱም በአካል ተገኝተው መሙላት እና መፈረም አለባቸዉ
-ከላይ የተጠቀሱትን ዝርዝሮች ለኢንሹራንስ አስፈላጊ በመሆናቸዉ ሁሉም ማሟላት አለባቸው ከላይ የተጠቀሱት ዝርዝሮች በሙሉ ካልተሟሉ መመዝገብ የማይቻል መሆኑን እንገልፃለን

ለተጨማሪ መረጃ የተወዳዳሪ ተወካዮቻችሁን ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን እናመሠግናለን
ቢኒያም ተስፋዬ 0911404600
ሚኪያስ ስዩም 0912341584

የአዲስ አበባ ከተማ ሞተር ስፖርት አሶሴሽን