🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'ከብረው ይቆዩን ከብረው በአመት ወንድ ልጅ ወልደው ሰላሳ ጥጆች አስረው ከብረው ይቆዩን ከብረው' | ህብረ ቀለማት ግጥሞች

"ከብረው ይቆዩን ከብረው
በአመት ወንድ ልጅ ወልደው
ሰላሳ ጥጆች አስረው
ከብረው ይቆዩን ከብረው"
ከሚል ምርቃት ላይ ፣ ጥያቄ ነጎደ
መክበር አይችልም ወይ ፣ ሴትን የወለደ ?
"የመበልፀግ ዘመን" ...
የሚል ጥቅሷን ይዛ ፣ በተነሳች ሀገር
አይቻላትም ወይ
ከሰላሳ በላይ ፣ እልፍ ጥጃ ማሰር?
።፣፣፣፣።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ሁልጊዜ ወንድ ልጅ ፣ እየተከበረ
ሁል ጊዜ ሰላሳ ፣ ጥጃ ከታሰረ
ድግግሞሽ እንጂ ፣ ይህን ምን ይሉታል
አዲስ ዓመት መጣ፣ አዲስ ነገር የታል?

መልካም አዲስ ዓመት